1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሲዳማ እና የደቡብ የክልሎች ጉብኝት

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 10 2017

ህዝቡ ቅሬታ የሚያቀርብባቸው የአገልግሎት አሰጣጥን ሥርዓትን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደሉት የአገልግሎት አሠጣጡን ለማዘመን በክልል ከተሞች መሶብ ተብሎ የሚጠራውን የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት እየዘረጋ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አሕመድ የሲዳማ እና የደቡብ የክልሎች ጉብኝት
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አሕመድ የሲዳማ እና የደቡብ የክልሎች ጉብኝት ምስል፦ Ethiopian Prime Minister Office

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሲዳማ እና የደቡብ የክልሎች ጉብኝት

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት መንግሥት የአገልግሎት አሠጣጡን ለማዘመን ከአዲስ አበባ ወጭ በሚገኙ ከተሞች መሶብ ተብሎ የሚጠራውን የአንድ መስኮት የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት እየዘረጋ ይገኛል ብለዋል ፡፡
በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ  የሀዋሳ የኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝተዋል ፣ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላም አከናውነዋል ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀዋሳ ፣ በአርባ ምንጭ እና በዎላይታ ሶዶ ከተሞችሲገቡ የአገር ሽማግሌዎችና የከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጉብኝታቸው ወቅት በሰጡት መግለጫ ህዝቡ ቅሬታ የሚያቀርብባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል እየተሠራ ይገኛል ብለዋል ፡፡ መንግሥት የአገልግሎት አሠጣጡን ለማዘመን በአዲስ አበባ መሶብ ተብሎ የሚጠራውን የአንድ መስኮት የኤሌክትሮኒክስ  ሥርዓት ከወራት በፊት ማስጀመሩ ይታወቃል ፡፡ አሁን ላይ አገልግሎቱን ከአዲስ አባባ ውጭ ባሉ የክልል ከተሞችም ለማስፋት  እየተሠራ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ “ የሀዋሳው አያያዙ ጥሩ ነው “ በማለት አድንቀዋል ፡፡

ቶዮ ለማኑፋክቸሪንግ ተስፋ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለማኑፋክቸሪንግ ማደግ  ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል የተባለውን  በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክየሚገኘውን የቶዮ የጸሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካንም ጎብኝተዋል ፡፡የቶዮ ኩባንያ ከወራት በፊት በቬይትናም በነበራቸው ጉብኝት ከኩባንያው ፕሬዚዳንት ጋር ባደረጉት ሥምምነት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ያስታወሱት አብይ “ ተጨማሪ ባለሀብቶች ወደ አገር እንዲገቡ የመጣውን በደንብ ማስተናገድና መያዝ ያስፈልጋል “ ብለዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በጉብኝቱ ወቅት እንደሉት የአገልግሎት አሠጣጡን ለማዘመን በክልል ከተሞች መሶብ ተብሎ የሚጠራውን የኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት እየዘረጋ ነው፡፡ምስል፦ Ethiopian Prime Minister Office

ቀጣይ ትኩረት

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተጠናቀቀ ባለው 2017 ዓ.ም የሲዳማ እና የደቡብ ኢትዮጵያን ክልሎች ሲጎበኙ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ፡፡ ዶቼ ቬለ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጉብኝት አስመልክቶ የግል አስተያየታቸውን የጠየቃቸው በሲዳማ ክልል በተቃዋሚ ፓርቲ አመራርነት የሚንቀሳቀሱት አቶ ገነነ ሀሰና ጉብኝቱ ለክልሉ በጎ መነሳሳት እንዳለው ጠቅሰዋል ፡፡ ክልሉ ሠፊ የተፈጥሮ መስህብና በርካታ የሰው ሀይል ጉልበት ያለው መሆኑን የተናገሩት አቶ ገነነ “ ነገር ግን እስከአሁን ቀደምሲል ከተሠሩ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በስተቀር  በገበታ ለአገር አይነት የሚሠሩ ፕሮጀክቶች አልታዩም ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀጣይ ይህ የልማት ዕድል ለክልሉ ይሰጣሉ የሚል ተስፋ አለኝ “ ብለዋል፡፡

 

ዘገባ ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሂሩት መለሠ
ፀሀይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW