1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የጤና ሁኔታ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 12 2004

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ የሃገሪቱን ህዝብ ማነጋገሩን ቀጥሏል ። አቶ መለስ በጠና መታመማቸውና ብራሰልስ ቤልጅየም መታከማቸው ከተለያዩ ምንጮች ተሰምቷል ። ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ዜና በማስተባበል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ

ምስል AP

 በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማስታወቁን የሃገር ውስጥና የውጭ የዚና ወኪሎች ዘግበዋል ። ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የጤና ሁኔታ ለማጣራት ዶቼቬለ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትንም ሆነ የቤልጂግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ሃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሂሩት መለሰ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መታመማቸውና ህክምና ላይ የመሆናቸው ጭምጭምታ መሰማት ከጀመረ ጥቂት ወራት ተቆጥረዋል ። የጤናቸው ሁኔታ አነጋጋሪነት ተጠናክሮ የቀጠለው ግን መለስ ሰኔ መጨረሻ ላይ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስበሰባ ላይ ሳያገኙና በኃላም ባለፈው ሳምንት እሁድና ሠኞ በተካሄደው የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሳይካፈሉ ከቀሩ በኋላ ነው ። ባላፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ደገሞ ብራስልስ ቤልጅየም ውስጥ በሚገኝ ሉክ በተባለ ሆስፒታል ታከሙ የተባሉት አቶ መለስ ሳያርፉ አልቀረም የሚሉ መላምቶችም መሰንዘር ጀምረው ነበር ። እነዚህን የመሳሰሉ የተለያዩ አስተያየቶች ከተለያዩ ምንጮች ሲሰሙ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የጤና ሁኔታ ምንም ነገር ሳይባል መታመማቸው በአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ ወቅት ነበር በይፋ የተነገረው። በአዲሱ የአፍሪቃ የልማት አጋርነት ወይም ኔፓድ ስበሰባ መክፈቻ ላይ የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማክ ሳሊ መለስ በጤና እክል ምክንያት አለመገኘታቸውን ካሳወቁ በኋላ

መለስ በኬንያው የላሙ ወደብምስል DW

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ብሉምበርግ ለተባለው የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ ምልልስ አቶ መለስ ከባድ ሳይሆን ቀላል ህመም እንዳጋጠማቸው ፣ እንደማንኛውም ስው ህክምና እንደሚያስፈልጋቸውና በቅርቡም እንደሚመለሱ ተናግረዋል ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤ.ኤፍ.ፒ ትንንት ባሰራጨው ዜና ግን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በጠና ታመው ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና እንድተደረገላቸው አንዳንድ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን አስታውቋል ። በዚሁ ዘገባ የ 57 ዓመቱ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ አስጊ መሆኑ ተጠቁሟል ። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምኦን፦ አቶ መለስ «በጠና አልታመሙም፤ ጤናቸውም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል» ማለታቸዉን ኤ,ኤፍ,ፒ በዘገባው ጠቅሷል ።

አቶ መለስ ብራሰልስ ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ስለመሆን አለመሆኑ በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማብራሪያ እንዲሰጠን ከዶቼቬለ የአማርኛዉ ክፍል ከትናንት በስተያ ላቀረብነዉ ጥያቄ፦-ኤምባሲዉ በኢሜይል በላከልን መልስ፤ አቶ መለስ በህክምና ላይ ናቸው መባሉን «ሃሰትና ስህተት» በማለት ገልፆ ታመሙ የሚለዉን ዜና «የሃሰት ታሪኮችን በማሰራጨት በተጠመዱና በተወሰኑ ወገኖች የተፈጠረ » በማለት አጣጥሎታል ።ኤምባሲው ይህን ቢልም የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ግን አቶ መለስ ለተወሰኑ ቀናት ብራሰልስ ከሚገኙት ዋና ዋና ሆስፒታሎች በአንዱ በግል መደበኛ ህክምና እንደተደረገላቸው ብራሰልስ የሚገኙ አንዳንድ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን አስታውቋል ።

ምስል picture-alliance/dpa

ዶቼቬለ ስለ መለስ የጤና ሁኔታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት መረጃ ለማግኘት ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። አቶ መለስ ብራሰልስ መታከም አለመታከማቸውን እንዲያረጋግጥ ዶቼቬለ ለቤልጂግ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጥያቄ ቢያቀርብም የመስሪያ ቤቱ ምክትል ቃል አቃባይ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት መግለጫ ሆነ ማስተባበያም እንደማይሰጡን ነው በስልክ የነገሩን ። ሆኖም ሪፖርተር ጋዜጣ ጠቅላይሚኒስትሩበመጪዎቹጥቂትቀናትውስጥየውጭሕክምናክትትላቸውንጨርሰውወደኢትዮጵያእንደሚመለሱየምንጮቹን ማንነት ሳይገልፅ ዘግቧል ። በዚሁ ዘገባ እንደተጠቆመውመለስ፣ወደአገራቸውሲመለሱወዲያውኑ ሥራ እንደማይጀምሩና ለተወሰኑጊዜያትካለባቸውከባድኃላፊነትርቀውዕረፍትእንዲያደርጉበሐኪሞቻቸውመመከራቸውንማንነታቸውን ካልጠቀሳቸው ምንጮችመስማቱን ሪፖርተር አስታውቋል ። የሕመማቸውምምክንያትምየሥራጫናመሆኑ ነው የተመለከተው ።ይህን መረጃ ግን ከመንግሥት ባለሥልጣናት ማረጋገጥ አልቻልንም ።

ጠቅላይሚኒስትሩሕክምናቸውንሲከታተሉበትየቆዩበትአገርለደኅንነታቸውሲባልእንዳይገለጽጠይቀዋል ያላቸውምንጮቹ ፣ከፍተኛየመንግሥትባለሥልጣናትመለስን ያሉበት ድረስ ሄደው እንደጎበኙዋቸውም ዘግቧል  ። ላለፉት 21 ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳትነት እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት አቶ መለስ ዜናዊ 20 ዓመት ሳይሞላቸው ነበር የህክምና ትምህርታቸውን አቋርጠው የደርግ መንግሥትን ለመውጋት የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ህወሀትን የተቀላቀሉት ።በ1981 ዓም የግንባሩን መሪነት የተረከቡት መለስ  ከዓመታት በኋላ ግንባሩ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተዋህዶ የመሰረተው ፣ የአሁኑ ገዥ ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዲግ ሊቀመንበርም ናቸው ።  በተቃዋሚዎችና በሰበዓዊ መብት ተሟጋቾች ሰብዓዊ መብትን በመጣስ የፕሬስ ነፃነትን በመጨቆንና ተቃዋሚዎችን በማዋከብ የሚወገዙት መለስ በደጋፊዎቻቸው ደግሞ ባለራዕይ መሪ ተደረገው ይወደሳሉ ። ለጊዜው የመለስ ህመም ምንነትም ሆነ ለምን ያህል ጊዜ ከህዝብ እይታ ተሰውረው እንደሚቆዩ ግልፅ አይደለም ። በአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እርሳቸውን ተክተው የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ናቸው ። አቶ ኃይለ ማርያም እስከ መቼ የእሳቸውን ቦታ ሸፍነው እንደሚሰሩም በግልፅ የታወቀ ነገር የለም ።

መለስ ዜናዊ ከምዋይ ኪባኪ ጋርምስል Reuters
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW