1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ጉብኝት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2016

የዐቢይን ጥረት በተለይ ተቃዋሚዎቻቸው በራሳቸው አገር ያለውን የሰላም ችግር እያነሱ የራሷ አሮባት አይነት ትችት ሲያቀርቡባቸው ተስምቷል።። በሌላ በኩል ደግሞ የሱዳን ቀውስ በኢትዮጵያም ሊያስክትል ከሚችለው ችግርና ኢትዮጵያም በአካባቢው ካላት ተስሚነትና ጥቅም አንጻር ጉብኝቱና ተንሳሺነቱ ተገቢና አስፈላጊም እንደሆነ በመግለጽ የሜክራከሩ አሉ ።

Äthiopien Premierminister Abiy Ahimed Diskussion
ምስል Office of Prime minister of Ethiopia

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ጉብኝት

This browser does not support the audio element.

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ  በሱዳን ፖርት ሱዳን ከተማ ተገኝተው ዋና ከተማ ካርቱምን ለቀው በዚያ ከከተሙት የሱዳን ፕሬዝዳንትና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሀን ጋር መወያየታቸው በዓለማቀፍና በተለይም በአረብ ሜዲያዎች ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ዜና ሆኖ ቆይቷል። ገበያው ንጉሴ ከብራስልስ ተጨማሪ ዘገባ አለው።

የሱዳን ጦርነት ያስክትለው ውድመትና ጉዳት

የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝድንት  ኦማርአልበሺር የመሰረቷቸው ሁለት ተገዳዳሪ የጦር ኃይሎች አዛዦች፤ የሱዳን ጦር ሀይሎች ዋና አዣዥ ጄነራል አልቡርሀንና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ዋና አዛዥ  ጄነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ፤ እሳቸው ከስልጣን  እንደተወገዱ ብዙም ሳይቆዩ በገቡበት የርስ በርስ ጦርነት ሱዳን ሙሉ በሙሉ በመፈረስ ላይ እንደሆነች እየተነገረ ነው። በጦርነቱ እስካሁን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የተገደሉ ሲሆን፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ያገሪቱ መሰረታዊ ልማትም ፈርሷል። በየል ዩንቨርስቲ መምህርና የሰባዊ መብቶች ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ሚስተር ናታኒል ሬይሞንድ በሱዳን  የደርሰው የተለየ እንደሆነ ነው የሚናገሩት፤ “ የምናውቃት ሱዳን እየሞተች ነው። አሁን የአካባቢው ሀይሎች ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚፋለሙብት የጦር ሜዳ ሁናለች” በማለት የደርሰውንና እየደረሰ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ገልጸዋል ። የመንግስታቱ ድርጅት የሰባዊ መርጃ ድርጅትም፤ በሱዳን  የደረሰው ሰባዊ ቀውስና ያንሻበበው የረሀብ እልቂት ከፍተኛ ሆኖ እያለ የሚደርሰው የርዳታ መጠን ግን ዝቅተኛ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን ደጋግሞ ሲገልጽ ተሰምቷል።የሱዳን ስደተኞች ወደ 3ኛ አገር መሄድ እንደሚፈልጉ ገለፁ


የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ጥረት  አነስተኛነትና የውጭ ጣልቃ ገብነት

አምሳ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት ሱዳን ከሰባት ያፍርካ አገሮች ጋርና ከአረቡ አለም ደግሞ በቀይባህር በኩል የምትዋሰን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላት አገር ብትሆንም፤ እራሷን እያፈረሰና ህዝቧን እየጨረሰ ካለው የርስ በርስ ጦርነት እንድትወጣ እየረዳ ያለ የቅርብም ሆነ የሩቅ ወዳጅ አገር ግን ቢያንስ ጎልቶ እንዳልታየ ነው የሚነገረው። እንደውም አንዳንድ ወዳጅና ጎረቤት አገሮች ለምሳሌ ግብጽ አልቡርሀንን በመደገፍ የተባበሩት አረብ ኤሚሪቶች ደግሞ ጄነራል ዳጋሎን  በመደገፍ በተዘዋዋሪ በጦርነቱ እንደሚሳተፉ ታማኝ የሆኑ የአለማቀፍ  ድርጅቶች በሚያወጣቸው ዘገባዎች አስታውቀዋል።

በሱዳን ጦርነት የኢትዮጵያ አቋም

ኢትዮጵያ ጄነራል ዳጋሎን ትደግፋለች በሚል በጀነራል አልቡርሀን ቡድን በኩል ቅሬታ ይሰማ እንድነበር የሚታወቅ ቢሆንም፤ ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማቸው ባደረጉት ንግግር ግን፤ ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም እንዲወርድ በገለልተኘት የራሷን ድጋፍ ከማድረግ ውጭ አንዱን ቡድን ለይታ እንደማተድግፍና ፖሊሲያዎም እንዳልሆነ  ግልጽ አድርገዋል።፡ ይህን ካሉ ጥቂት ቀናት ብኋላም ባለፈው ማክሰኞ  ካርቱምን ለቀው ግዚያዊ መቀመጫቸውን በጊዚያዊነት ፖርት ሱዳን ያደረጉትን ጂነራል አልብርሀንን እዚያው ድረስ በመዝለቅ እንዳገኟቸውና  የበኩቸውን የስላም ሀሳብም እንዳቀረቡላቸው ተገልጿል። ጉብኝቱ ጤቅላይ ሚኒስተር አቢይን፤ በሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ከተጅመረ ወዲህ ሱዳንን በመጎብኘት  የመጀመሪያው ያገር መሪ ያደርጋቸው ሲሆን፤ ይህም ባለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን በሰፊው ተዘግቦ ታይቷል።

ጀነራል አል ቡርሀን ዘንድሮ በመስከረም 2023 ዓ.ም.በተመድ ንግግር ሲያደርጉ ምስል Craig Ruttle/AP/picture alliance

የሁለቱ መሪዎች የጋራ ውይይት

ሁለቱ መሪዎች ከውይይታቸው በኋላ ቀድሞ ቲውተር ባሁኑ ኤክስ ገጾቻቸው በየበኩላቸው ጉብኙት በወዳጅነት መንፈስ የተካሄደና ፍሪያማ እንድነበር አስታውቀዋል። የሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ባወጣው መገልጫም ጉብኝቱ የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት ጥልቅ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ማለቱ ተዘግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስተሩ ጉብኝት የተነሳበት ትችትና የተሰጡ አስተያየቶች

ይህን የጠቅላይ ሚኒስተር አቢይን ጥረት በተለይ ተቃዋሚዎቻቸው በራሳቸው አገር ያለውን የሰላም ችግር መሰረት አድርገው  የራሷ አሮባት አይነት ትችት ሲያቀርቡባቸው ተስምቷል።። በሌላ በኩል ደግሞ የሱዳን ቀውስ በኢትዮጵያም ሊያስክትል ከሚችለው ችግርና ኢትዮጵያም በአካባቢው ካላት ተስሚነትና ጥቅም አንጻር ጉብኝቱና ተንሳሺነቱ ተገቢና አስፈላጊም እንደሆነ በመግለጽ የሜክራከሩ አሉ ። በብርታኒያ በደንዲ ዩንቨርስቲ ያዶክትሬት ተማሪ የሆነውና የፖልቲካ ተንታኙ ደቡብ አፍርካዊው ሙሳ ሙዱንጌ ይህንን ሀሳብ ከሚጋሩት አንዱ ነው። “ ይህ ትልቅ ትርጉም ያለው ስብሰባ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ምናልባትም  በዚያ አገር ቢያንስ የኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል እድል ሊፈጥር ይችላል”ብሏልየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ በኢጋድ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ እንዲሳተፉ መጋበዛቸውን አስታወቁ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በአረብ ሜዲያዎች

ይህን የጠቅላይ ሚኒትሩን የሱዳንን ጉብኝት በሚመለክት  የአረብ ሜዲያዎች ባጠቃላይ  እንዴት እንደዘገቡትና እንደሸፈኑት  እንዲገልጽልን  በተለይ በአባይ ጉዳይ የአረብ ሜዲያዎችን በመከታተልና ለህዳሴው ግድብ በሞሟገት  የሚታወቀውን ኢስታዝ ጀማል በሽሪንም በስልክ ጠይቄው ነበር
 
ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ጫኔ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW