1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በትግራይ ክልል ይደረጋል ስለተባለው ምርጫ የተደረገው ዉይይት እና አንድምታው

ሰለሞን ሙጬ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 19 2019

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማከናወን ስለሚቻልበት ኹኔታ ትናንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪክ ድርጅቶች ጋር ተወያይቷል።

Äthiopien Mekelle 2026 | Anhänger begrüßen den früheren Tigray-Regierungschef Getachew Reda
ምስል፦ Filmon Equar Hailu/AP Photo/picture alliance

የትግራይ ክልል የምርጫ ጉዳይ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምልከታ

This browser does not support the audio element.

 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫ ማከናወን ስለሚቻልበት ኹኔታ ትናንት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪክ ድርጅቶች ጋር ተወያይቷል።

አንዳንድ አገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅቶች በክልሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ በመጥቀስ ሀሳቡን እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

የፌዴራል መንግሥት በክልሉ አገልግሎቶችን መመለስና ሕዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የፈጠነ ምርጫ ማድረግ ላይ ማተኮሩን ይፋ አድርጓል።

ህወሓትን ጭምር ያካተተው የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ትናንት ባወጣው መግለጫ ግን ለእያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ የትግል ጥሪ አድርጓል።

በትግራይ ክልል በህወሓትና በፌዴራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ባለፈው ዓመት ጠቅላላ ምርጫ ባለመደረጉ ክልሉ በሕዝብ ተወካዮች እና በፌደሬሽን ምክር ቤቶች ምንም ውክልና የለውም።

የኢትዮጵያብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም. በትግራይ ክልል መደረግ ስላለበት ምርጫ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተወያይቷል። 

ፌዴራል መንግሥት በክልሉ አገልግሎቶችን መመለስና ሕዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የፈጠነ ምርጫ ማድረግ ላይ ማተኮሩን ይፋ አድርጓል።ምስል፦ Office of the Prime Minister-Ethiopia

በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የኢሕአፓ ዋና ፀሐፊ ምስጢረ ሥላሴ ታምራት ከውይይቱ ምርጫው በቅርብ ጊዜ እንደሚከናወን መገንዘባቸውን ገልፀዋል። ሆኖም ፓርቲያቸው ክልሉ አሁን ለምርጫ ምቹ ኹኔታ እንደማይታይበት እንደሚያምን ገልፀዋል።

"አሁንም በጦርነት ውስጥ ያለ ሕዝብ ነው። ሕዝቡ ያለበት ኹኔታ መታየት ያለበት ነው። በዚህ ኹኔታ የሚደረግ ምርጫ ከዲሞክራሲም፣ ከሰብአዊ ኹኔታም አንፃር ብትመዝነው ካለፈው ምርጫ የተለየ ነገር አይኖረውም።"

የውይይቱ ተሣታፊዎች ምርጫው ተገቢ እንደሆነ ቢያምኑም አስቻይ ኹኔታን ጨምሮ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች መኖራቸውን እንዳሳሰባቸው ቦርዱ ገልጿ። ዛሬ ከክልሉ ባለአደራ አስተዳደር መሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫው የመንግሥታቸው አንዱ ዐቢይ ጉዳይ መሆኑን በሀሙሱ የፓርላማ ውሎ ላይ አንስተውታል።

"የትግራይ ሕዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ረጅም ዓመት ታግሏል፣ ያ መብቱ እንዲከበርለት የፈጠነ ምርጫ ማካሄድ፣ ለልማት ማዘጋጀት፣ ያ እየሆነ እያለ የተቸገሩ ሰዎች ካሉ ኢትዮጵያ ሀገራቸው ማገዝ የምትችልበትን መንገድ መከተል ነው።"

የውይይቱ ተሣታፊዎች ምርጫው ተገቢ እንደሆነ ቢያምኑም አስቻይ ኹኔታን ጨምሮ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ ብለዋልምስል፦ REUTERS

በዚሁ የምርጫ ጉዳይ ላይ በዚሁ ሳምንት ያነጋገርናቸው በትግራይ ክልልከሚንቀሳቀሱየፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የትንሳኤ 70 እንደርታ እና የሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ፓርቲዎች የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ይህንን ብለው ነበር።

"ምርጫ ሲደረግ ተሳታፊ እንሆናለን።"  "ትግራይ ያለችበት የፀጥታ ኹኔታ በጣም አሳሳቢ ነው። [ምርጫ] ይደረጋል ወይ የሚለውን ልተወው እና ግን [ቦርዱ] እያነጋገረን ነው።"

ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ በትግራይ ክልል ምርጫውን መቼ ሊያከናውን እንዳቀደ በግልጽ አልጠቀሰም። በፌዴራል መንግሥት ላይ ብርቱ ወቀሳ ያነሳው ህወሓትን ጭምር ያካተተው የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ የተባለ ስብስብ ትናንት ባወጣው መግለጫ ለእያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ የትግል ጥሪ አድርጓል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

 

 

Edited by:Tamirat Dinssa Geleta ታምራት ዲንሳ ገለታ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW