1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ አብይ አስተዳደር አንድ መቶ ቀናት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2010

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ የአንድ መቶ ቀናት የሥራ ስኬቶችን የተመለከተ አጠቃላይ መግለጫ ሰጠ።

Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

የዲፕሎማሲ ስኬቶች ተመዝግበውበታል

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ስልጣን ከተረከቡ ዛሬ 100 ቀን ሆናቸው። በዚሁ ጊዜ በወሰዷቸው በርካታ ርምጃዎች  ለምሳሌ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ታይተው የነበሩ ተቃውሞና ግጭቶች እንዲያበቁ በማድረግ ውስጣዊ መረጋጋት አስገኝተዋል፣  የፖለቲካ እስረኞች ተፈተዋል፣ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቷል። ከዚሁ ባሻገርም በጠቅላይ ሚንስትሩ ከፍተኛ ጥረት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ከተለያዩ ሀገራት ጋር ብዙ  የተሳካ ዲፕሎማሲያዊ ስራ የተሰራበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።  ከዚሁ መካከልም ላለፉት ሀያ ዓመታት ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት ካላንዳች የውጭ ሸምጋይነት በራሳቸው በሁለቱ ሀራት ህዝቦች እና መሪዎች ፍላጎት መልሶ የታደሰበት የሰላም ስምምነት ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የደረሱትን ስምምነት ተግባራዊ በማድረጉ ረገድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጹንም አቶ መለስ አክለው ተናግረዋል። በጋዜጣዊ ጉባኤው ሌሎችም ጉዳዮች መነሳታቸው ተገልጿል።

ምስል Yemane G. Meskel

 

 

አርያም ተክሌ/ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW