1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐብይ ቀጣይ በፍቅር የመደመር ጉዞ በአውሮጳ  

ዓርብ፣ ጥቅምት 2 2011

በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ እና ሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ዝግጅት ኮሚቴ አስተባባሪዎች ስለ ፍራንክፈርቱ የዶክተር ዐብይ አቀባበል መረሃ- ግብር ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል።

Frankfurt - Premierminister Dr. Abiy Ahmaed trifft auf Äthiopische Diaspora
ምስል DW/E. Fekade

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ኮሚቴ መግለጫ

This browser does not support the audio element.

" የጥላቻ ግንቡን እናፍርስ የፍቅር እና የአንድነት ድልድዩን እንገንባ " በሚለው የለውጡ ኃይል መርህ በያዝነው ወር ኦክቶበር 31,2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በመላው አውሮጳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ተገናኝተው ለሚያደርጉት ታሪካዊ ጉባኤ የተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ ኢትዮጵያዊው በነቂስ ወቶ ለለውጡ ያለውን አጋርነት እንዲያሳይም ጥሪውን አስተላልፏል። ዛሬ በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በተካሄደ የውይይት እና የምክክር መድረክ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ኩማ ደመቅሳ እና ሌሎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ዝግጅት ኮሚቴ አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሂደት በዉጭ ስለሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ  ሚና እና ስለ ፍራንክፈርቱ የዶክተር ዐብይ አቀባበል መረሃ- ግብር ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው ዘጋቢያችን እንዳልካቸው ፈቃደ ተከታዩን ዘገባ ከስፍራው ልኮልናልል። 

እንዳልካቸው ፈቃደ 
አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW