የጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ
ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011ማስታወቂያ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፣በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አማካይነት ዛሬ ናይሮቢ ውስጥ ከተወያዩ በኋላ በመካከላቸው ሰላም ለማውረድ መስማማታቸውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው በተነሳ የባህር ወሰን ውዝግብ ምክንያት ለአንድ ወር ያህል ውጥረት ውስጥ ነበሩ። የሁለቱን ሀገራት ውይይት ያመቻቹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሰሞኑን ከኬንያ ከኤርትራና ከደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋርም በቀጠናው ሰላም እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይም መክረዋል። ስለ ኬንያ እና ሶማሊያ ስምምነት እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሚና እንዲሁም ስለ ሰሞኑ የቀጣናው መሪዎች ምክክር ፋይዳ በጅጅጋ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አቶ ሙሳ አደምን ስቱድዩ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ