1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜሎኒ የልማት እቅድ እና ፈተናዎቹ

ሰኞ፣ ጥር 20 2016

የጣሊያን መንግሥት ለአፍሪቃ ባዘጋጀው የልማት እቅድ ላይ የተወያየ ጉባኤ ዛሬ ሮም ውስጥ ከአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች ጋር ተካሄደ ። የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ከተወሰኑ የአፍሪካ መሪዎች ጋር በተለይም ከአፍሪካ ቀንድ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Italien-Afrika Gipfel in Rom
ምስል Remo Casilli/REUTERS

የሜሎኒ የልማት እቅድ እና ፈተናዎቹ

This browser does not support the audio element.

በጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የተጠራዉ የጣሊያን-አፍሪካ የሁለት ቀናት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሮም መካሄድ ጀምሯል። በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኤርትራ መሪዎችን ጨምሮ የ23 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የመንግሥታት ተወካዮች ተገኝተዋል። የአውሮፓ ህብረት ተቋማት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ከተሳታፊዎች መካከል ይገኙበታል። የጣልያንዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ፍልሰትን በጋራ ለማስቆም ይረዳል ያሉትን አዲሱን የጣሊያን እቅድ ይፋ አድርገዋል።  ፍልሰትን ያስቆማል ካሉበትየመፍትሔ ሀሳብ ባሻገር ሜሎኒ አፍሪቃ ለአውሮጳ ዋነኛዋ ኃይል አቅራቢ እንድትሆን ያስችላታል ያሏቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች በዝርዝር ማስተዋወቃቸው ተዘግቧል።

 የኢጣልያ እቅድ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽንን ብዙም አላረካም። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር ኢጣልያ እቅዷን ይፋ ከማድረጓ አስቀድሞ እኛን ማማከር ነበረባት ሲሉ ተችተዋል።

የጣሊያን አፍሪቃ ጉባኤ በሮም ምስል Remo Casilli/REUTERS

ቃል ከመግባት ወደ ተግባር መሸጋገር አለብን ያሉት ፋኪ ማሃማት መቼም ተግባራዊ ሆነው በማያውቁ ቃሎች ደስተኛ ልንሆን አንችልም ሲሉም ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። ምክር ቤት ያልተቀበለው የፈረንሳይ የስደተኞች ሕግ ማሻሻያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሚሎኒ ከተወሰኑ የአፍሪካ መሪዎች ጋር በተለይም ከአፍሪካ ቀንድ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW