የጥላቻና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች በኢትዮጵያ
እሑድ፣ ግንቦት 7 2014
ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ቀንማክሰኞ፤ ሚያዝያ 25 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ተከብሯል። የፕሬስ ነጻነትን የማስጠበቅ እና ጥላቻን የሚያጭሩ ንግግሮችን የመቆጣጠር ጉዳይ ግን ዛሬም ድረስ አነጋጋሪ ነው። ኢትዮጵያ ግለሰብንም ሆነ ኅብረተሰብን ለጥቃት የሚያጋልጡ ንግግሮችን ሊቆጣጠር ይችላል የተባለለትን «የጥላቻ ንግግር ሕግ» አርቅቃ ካጸደቀች ረዘም ያሉ ጊዜያት አልዋል። የጥላቻ እና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ግን አሁንም ድረስ አልጠፉም። አንዳንድ ጊዜ ንግግሮቹ አንድን ብሔር እና ተናጋሪው የእኔ ከሚለው ቡድን ውጪ ያለውን አካል ሲያንኳስሱ ብሎም ለጥቃት ሲያነሳሱ ይስተዋላል። ከሰሞኑ እንዲህ ያለው ንግግር በተለያዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ መቃቃር እንዲኖር፤ በዚያው ልክም ጥፋት እንዲከሰት ሰበብ መሆኑ ይነገራል። በሌላ ጎኑ እነዚህን ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ለመቆጣጠር የሚወጡ ሕግጋት ጋዜጠኞችን እና ተቺዎችን ለጥቃት እንዳያጋልጡ ሲሉ ስጋታቸውን የሚሰነዝሩም አሉ።
የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር በሚል የመናገር ነጻነት እንዳይደፈለቅ ስጋታቸውን የሚገልጡ አሉ። በመናገር ነጻነት እና በግጭት ቀስቃሽ ወይንም አባባሽ ንግግሮች መካከል ያለው ድንበሩ ወይንም መስመሩ የቱ ጋር ነው ይላሉ?
ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭትን ሊያባብሱ የሚችሉ ጥላቻን አጪያሪ እና አንኳሳሽ ንግግሮች ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችም በውይይቱ ተነስተው ሰፊ ትንታኔ ተሰቶባቸዋል።
ሙሉውን ውይይት በድምፅ በማገናኛው ማድመጥ ይቻላል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂቱት መለሰ