የጥምቀት በዓልና ባህላዊ ክዋኔ በወሎ
ቅዳሜ፣ ጥር 10 2017በጥር ወር በዓላት መካከል አንዱ የሆነዉ የጥምቀት በዓል ከሀይማኖታዊ አከባበር ባሻገር በወሎ ባህላዊ ክዋኔ በጉልህ ይታይበታል። ቀጭን ዱላ ሸልሞ ጠባቃ ሎሚ መርጦ ዉሃ አጣጩን ለማግኘት ወደ ጥምቀት በዓል የሚመጣ ጢነኛ በርካታ ነዉ አቶ ሰሎሞን ይመር በዚሁ መልክ ነዉ ሚስታቸዉን ያገቡት።
«እኔ አሁን ለምሳሌ ሚስቴን ያገባኃት ጥምቀት ላይ ነዉ ሎሚ በዘንግ አቀበልኳት ከዚያ በኃላ ተገናኘን ተግባባን በያመቱ ብዙ ጥምቀት አክብረን ጊዜዉ ሲደርስ ተጋባን የታወቀች መተጫጫናት ሎሚ»
በጥምቀት ወቅት ከወንድ ጢነኛ ሎሚ የተቀበለች የከንፈር ወዳጂ ክብሯን ሊጠብቅ እስከ ሰርጓ ሊያደርስ ቃል የሚገባበት ማህበራዊ ህግ ነዉ ነዉ ይላሉ አቶ ተፈሪ አስፋዉ ።
«ከንፈር ወዳጂ ክብሯን ጠብቆ እስከምታገባ ድረስ በክብሯ እንድትቆይ ትልቅ ከበሬታ ይሰጣል ለሷ ያቀብላል እርሷም ካልፈለገችዉ በስድብ ትዘፍነዋለች»
የሽማግሌ ባር ስበላዉ ስጠላዉ
ወደቀብኝ መሰል ዘፈፍ አለ ጥላዉ ትላለች አትፈልገዉም ከፈለገችዉም ስቃ በጮረቃ ሎሚዉን በስቶ አርቲ ያደርግበታል አርቲጋር ይሰጣታል።
ሳዱላዎች የተመረጠ ለብሰዉ አርቲና አሽኩቲ ይዘዉ ሹርባ ተሰርተዉ ለጥምቀት በዓል አደባባይ ሲወጡ ከጢነኛ ሎሚ ያልደረሳት ሳዱላ ካለች ማኩረፍ ልማዷ ነዉ ይላሉ ወይዘሮ አረጋሽ ደምሴ
«ልጆቹ በጣም በደስታ ነዉ የሚቀባበሉት ያልመጣላት አኩርፋ ትዉላለች አርቲና ሎሚ ያልተቀበለችዉ የመጣላቸዉ ተቀብለዉ ይጠቀሙበታል እጆሯቸዉ ላይ ሎሚዉን በጉያቸዉ ዉስጥ ይዘዉ ያሸታሉ ጆሯነዉ ላይ አርገዉ ፀጉራቸውን ሹሩባ ተሰርተዉ በጣም እየነሰነሱ ፀጉራቸዉን ይጨፍራሉ አብረዉ»
በጥምቀት ወቅት አሆላሎ እያሉ ለመጫወት አደባባይ የሚወጡ አዲስ ያገቡ አልያም ልጃገረድ ሴቶች ናቸዉ በጨዋታዉ ላይ እንዲሳተፉ የሚፈቀድላቸዉ።
«ሴቶቹ ባዲስ ያገቡ ወይም ያላገቡ ልጃ ገረዶች ፀጉራቸዉ የራሱ ጌጥ አለዉ በዚያ ነዉ የሚዘፍኑት ትልልቅ ሴቶች አይገቡም በዚያ ላይ መተጫጨት አለ መፈላለግ አለ እናም እዚያ ካያት ቤተሰብ ልኮ እንዲያገባት ይደረጋል»
በጥምቀት ጨዋታ ቆንጆዉ ሁሉ አምሮ በሚወጣበት ዕለት ለምን የሎሚ ፍሬ ለፍቅር መግለጫ ሆና ተመረጠ
«ሎሚ በባህላችን መሰረት ጥሩ ሽታ ያለዉ ልዮነት መልክ ያላት ነገር ስለሆነች ናትራ ከሚባል ነገር ጋር አንድ ላይ አቀላቅለን ለመታጨትና እዉቅና ለማግኘት ያገለግላል ሽታዋም ጥሩ ነዉ ናትራ እንጨምርበታለን እዛ ዉስጥ ለመስጠትና ለማቀበል አማሪ። የምናቀብላትን ልጂ የምትመስል ነገር ስለሆነች ተምሳሌቷ ጥሩ በመሆኑ ተመራጭ ነች»
ለጥምቀት በዓል አሆላሎ እያለች ልትጫወት የወጣች ልጃገረድ ከሁለት ወንድ ሎሚ መቀበል አትችልም ምክንያቱ ደግሞ ከቤተሰብ የሚያደርስ ግጭት ያመጣል ተብሎ ስለሚፈራ ነዉ።
«ከሁለት ሰዉ ሎሚ እንዳይቀበሉ ወላጆቻቸዉ ሳይሆኑ ታላቅ እህቶቻቸዉ ያክስት ልጂ ያጎት ልጂ በዚያ ጨዋታ ዉስጥ ያለፉ ይመክሯቸዋል።
በጥር ወቅት በጥምቀት በቃና ዘገሊላ በአስተርዬ ማርያምና ሌሎች በአላቶች የወሎ ሳዱላና ጢነኛ ሎሚን ለፍቅር መግለጫ አድርገዉ ሦስት ጉልቻ ለመመስረት ይበቃሉ።
ኢሳያስ ገላው
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር