እምነትአፍሪቃ
የጥምቀት በዓል አከባበር በአዲስ አበባ
ረቡዕ፣ ጥር 11 2014
ማስታወቂያ
የጥምቀት ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ጃንሜዳ በሚገኘው ዋናው እና በሌሎችም ባህረ ጥምቀቶች ከፍ ባለ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ ውሏል። በአዲስ አበባ ከተማ 74 ጥምቀተ-ባህራት ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ዋናው የጃንሜዳው ነው። በከተማዋ 270 አብያተ ክርስትያናት መኖራቸው ተገልጿል። ከእነዚህም የ12ቱ አብያተ ክርስትያናት ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ጃን ሜዳ ያድራሉ። በጃንሜዳው የጥምቀት ክብረ በዓል ሥነ ሥርዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያሪክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በኅመም ምክንያት ባይገኙም በተወካያቸው ብጹእ አቡነ አረጋዊ በኩል መልእክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካሏት ዐበይት የአደባባይ ክብረ በዓላት አንዱ የሆነው ጥምቀት በልዩ መስህቡ እና የአከባበሩ ድምቀቱ በዓለም አቀፍ ቅርስነት ተመዝግቧል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ