1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጦርነት ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ

ሰኞ፣ ጥር 5 2017

በሰልፉ ምክንያት በርካታ የመቐለ ከተማ ጎዳናዎች ዛሬ ተዘግተው የዋሉ ሲሆን፥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፖሊስ ሐይልም በከተማዋ ተሰማርቷል። የሰልፊ አስተባባሪዎች ሰልፉ በሚፈልገው ሁኔታ እንዳይካሄድ በርካታ እንቅፋቶች እየተከወኑ ነው በማለትም ቅሬታቸው ይገልፃሉ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስቱ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ሓላፊነቱ ይወጣ ብሏል።

Äthiopien Mekelle 2025 | Proteste von Vertriebenen des Tigray-Krieges
በሰልፉ ምክንያት በርካታ የመቐለ ከተማ ጎዳናዎች ዛሬ ተዘግተው የዋሉ ሲሆን፥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፖሊስ ሐይልም በከተማዋ ተሰማርቷል። ምስል Million Hailesilassie/DW

የጦርነት ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ

This browser does not support the audio element.

በመቐለ የሚገኙ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። ተፈናቃዮቹ መንግስት ረስቶናል ብለዋል። ፅላል በተባለ ሲቪክ ማሕበር አዘጋጅነት ዛሬ የተጀመረው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ የመቐለ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች በመዝጋት ጭምር ለቀጣዮቹ ሶስት ቀናት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በዚህ እርምጃቸው የመንግስት እና የሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያገኙ እንዲሁም ወደቀዬአቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ሊፈጠር ይጠብቃሉ። ግዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ሰልፉ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የፌደራል መንግስቱ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ሓላፊነቱ ይወጣ ብሏል።

ትግራይ፤ ዛሬም ድንኳን ዉስጥ የሚኖሩት የጦርነት ተፈናቃዮች

ዛሬ የመቐለ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች እንዲዘጉ ምክንያት የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉት በመቐለ ያሉ ተፈናቃዮች ከቀዬአቸው ተለይተው እየኖሩት ያለው ሕይወት የከፋ ብለውታል። እነዚህ በዋነኝነት ከምዕራብ ትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች፣ ከኤርትራ ከሚዋሰኑ ወረዳዎች እንዲሁም ሌሎች የሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች በዋነኝነት የተፈናቀሉ ዜጎች ከቦታቸው ከተፈናቀሉ 1523 ቀናት እንዳለፉ ገልፀዋል።

ፅላል በተባለ ሲቪክ ማሕበር አዘጋጅነት ዛሬ የተጀመረው ይህ የተቃውሞ ሰልፍ የመቐለ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች በመዝጋት ጭምር ለቀጣዮቹ ሶስት ቀናት እንደሚቀጥል ተገልጿል።ምስል Million Hailesilassie/DW

መንግስት ጉዳያችን ችላ ብሏል፣ በመጠልያ ተረስተን እንድንኖር ተፈርዶብናል፣ ይበቃናል ሲሉ ድምፃቸው አሰምተዋል። በመቐለ ሮማናት አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው እና ለቀጣዩቹ ሶስት ቀናት ይዘልቃል በተባለው ሰልፍ፥ በእድሜ የገፉ ተፈናቃዮች፣ ወጣቶች፣ ጥያቄአቸው እንደሚደግፉ የገለፁ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች እና ሌሎች እየተሳተፉበት ነው።

የትግራይ ተፈናቃዮች ስሞታ

በሰልፉ ምክንያት በርካታ የመቐለ ከተማ ጎዳናዎች ዛሬ ተዘግተው የዋሉ ሲሆን፥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፖሊስ ሐይልም በከተማዋ ተሰማርቷል። የሰልፊ አስተባባሪዎች ሰልፉ በሚፈልገው ሁኔታ እንዳይካሄድ በርካታ እንቅፋቶች እየተከወኑ ነው በማለትም ቅሬታቸው ይገልፃሉ።

የጦርነቱ ተፈናቃዮች ዛሬ በመቀሌ ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍምስል Million Hailesilassie/DW

ወደ ቀያቸው የተመለሱ የትግራይ ተፈናቃዮች ደስታና መመለሱ የዘገየባቸው ተፈናቃዮች ቅሬታ

ተፈናቃዮቹ ለመመለስ ከፌደራል መግግስቱ ጋር መግባባት እንደሚያስፈልግ ይሁንና እስካሁን በሚፈለገው ደረጃ ይህ ውጤት እንዳላስገኘ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በተደጋጋሚ ይገልፃል። ግዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ሰልፉ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ የፌደራል መንግስቱ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ሓላፊነቱ ይወጣ ብሏል።

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ለመመለስ ለሚደረግ ጥረት ማስፈፀሚያ ዝርዝር እቅድ መውጣቱ፥ ሂደቱ ለማስፈፀም ደግሞ 2 ነጥብ 1 ቢልዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በቅርቡ ይፋ ማድረጉም ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW