1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለማችን ጦር መሳርያ ሽያጭ አገሮች

ሰኞ፣ መጋቢት 2 2016

የጎርጎረሳዉያን 2023 ዓመት የዓለም የጦር መሳርያ ዝዉዉርና ሽያጭን በተመለከተ፤ በዓለማችን የጦር መሳርያ ንግድ ዩናይትድ ስቴትስ አንደኛ፤ በሁለተኛ ፈረንሳይ ፤ ሦስተኛ ሩስያ፤ አራተኛ ቻይና፤ አምስተኛ ጀርመን ስድስተኛ ጣልያን ፤ ሰባተኛ ኢጣልያ ፤ እንዲሁም ስምንተኛ ታላቅዋ ብሪታንያ መሆናቸዉ ዓለም አቀፉ ተቆጣጣሪ ተቋም አስታወቀ።

Militärübung in Japan I Japanese F 15
ምስል USAF/Planet Pix/ZUMA/picture alliance

በዓለማችን በጦር ምርት እና ንግድ ቀዳሚዋ የሆነችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ዘንድሮም  ቀዳሚዉን ስፍራ ይዛ መቀጠልዋን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም «SIPRI» ዛሬ ይፋ ባደረገዉ የጥናት ዘገባ አመለከተ። የምርምር ተቋሙ በባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2023 ዓመት የዓለም የጦር መሳርያ ዝዉዉር እና ሽያጭን በተመለከተ ባካሄደዉ ጥናት፤ በዓለማችን ለሌሎች ሃገራት የጦር መሳርያን አምርቶ በመሸጥ ዩናይትድ ስቴትስ አንደኛ፤ በሁለተኛ ደረጃ ፈረንሳይ ፤ ሦስተኛ ሩስያ፤ አራተኛ ቻይና፤ አምስተኛ ጀርመን ስድስተኛ ጣልያን ፤እንዲሁም ሰባተኛ ታላቅዋ ብሪታንያ ሲል በመዘርዘር አስቀምጥዋል። ሩስያ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻፀር ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት 2023 የመሳርያ ንግድን በመቀነስዋ በመዘርዝሩ ተቀምጣ ከነበረችበት ደረጃ በአንድ ዝቅ ብላለች። ፈረንሳይ በበኩልዋ መሳርያን በማምረት እና ለሌሎች ሃገራት መሸጥዋን በመጨመርዋ በዓለማችን ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ሁለተኛዋ የዓለማችን የጦር መሳርያ ንግድ ያካሄደች ሃገር ናት ሲል ድርጅቱ ይፋ ባደረገዉ መዘርዝር አስቀምጧታል። ሩስያ ቀደም ባሉት ዓመታት በጦር መሳርያ ሽያጭ ሁለተኛ ቻይና እና ጀርመን ሦስተኛ እና አራተኛ ሆነዉ ተቀምጠዉ ነበር። ከዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ንግድ መካከል 42 በመቶ ድርሻዉን የምትይዘዉ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለማችን ቀዳሚዋ የጦር መሳርያ ሻጭ ሃገር በመሆን መቀጠልዋን ድርጅቱ ይፋ አድርጔል። ይሁን እና ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት 2023 የዓለም የጦር መሳሪያ ንግድ በ 3.3 በመቶ መቀነሱን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ እና SIPRI የተሰኘዉ የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም ይፋ አድርጓል።  


አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW