የጦር ሥልጠና ለፔሽመርጋ ተዋጊዎች በጀርመን7 መጋቢት 2007ሰኞ፣ መጋቢት 7 2007የጀርመን ብሔራዊ ጦር በሰሜን ኢራቅ በ«አይ ኤስ» ወይም በእስላማዊው መንግሥት አንፃር ለሚዋጉት የኩርድ ፔሽመርጋ ተወላጆች የጦር ስልት ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፣ ጦሩ ለፔሽመርጋ ተዋጊዎች ሥልጠና ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አለመሆኑን የጀርመን መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል Bundeswehr/Florian Räbel/dpaማስታወቂያ ለሥልጠና በጀርመን የሀምልቡርግ ከተማ የሚገኘው ሁለተኛው የፔሽመርጋ ተወላጆች ቡድን ከውጊያ ስልት ጎን የጦር መሳሪያ መፈታታት እና መግጠም፣ የተሰበሩ የጦር ተሽከርካሪዎችን መጠገን ፣ በተለይም፣ የተቀበሩ ፈንጂዎችን ፈልጎ ማምከንን እና በፀረ ታንክ ሮኬት በትክክል መጠቀም የሚያስችለው ትምህርት ይሰጠዋል። ለቮልፍጋንግ ዲርክ/ይልማ ኃይለሚካኤል አርያም ተክሌ ተክሌ የኋላ