የጨፌ ኦሮምያ ጉባኤ
ሰኞ፣ ሐምሌ 20 2012
ማስታወቂያ
የኦሮምያ ምክር ቤት ጨፌ ኦሮምያ ቅዳሜ እና እሁድ በአዳማ ያካሄደው የ5 ተኛ ዘመን 5ተኛ ዓመት 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ ትናንት ተጠናቋል። በተገባደደው ዓመት አፈጻጸም፣በመጪው ዓመት በጀት እና እቅድ ላይ የተወያየው ጉባኤው የክልሉን የ2013 ዓም በጀት ሹመቶችንና አዋጆችንም አጽድቋል።በጉባኤው ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት መልስ ሰጥተዋል። ጥያቄ ከቀረባቸው ጉዳዮች መካከል በዓመቱ ክልሉን የፈተነው የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም የአዲስ አበባና የኦሮምያ ወሰን ይገኙበታል።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ