1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጳጉሜ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 3 2017

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በግብጽ ቡድን 2 ለ0 የተሸነፈው ቡድኑ ላይ በግብፅ ደጋፊዎች የስነስርዓት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ለፊፋ ክስ አቅርቧል ።ል ርቆት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በመጥፎ ውጤት የጀመረው የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የሰሜን አየርላንድ ቡድንን በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል ።

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ሰሜን አየርላንድን 3 ለ1 አሸንፏል
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ሰሜን አየርላንድን 3 ለ1 አሸንፏል ። የቅዳሜው ድል ዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ለማለፍ ጊዜያዊ እፎይታ ነው ምስል፦ Dean Mouhtaropoulos/Getty Images

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በግብጽ ቡድን 2 ለ0 የተሸነፈው ቡድኑ ላይ በግብፅ ደጋፊዎች የስነስርዓት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ለፊፋ ክስ አቅርቧል ። በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድንን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ የተካተተበት ቃለ መጠይቅም ይኖረናል ። ድል ርቆት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በመጥፎ ውጤት የጀመረው የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የሰሜን አየርላንድ ቡድንን በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል ። 

በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ

በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ነገ ወደ ውድድር ስፍራው እንደሚያቀና ተዘግቧል ። ከውድድሩ ቀደም ብሎ በ1500 ሜትር ተፎካካሪዎች ላይ ለውጥ የተደረገ መሆኑ ተገልጧል ። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ዛሬ አዲስ አበባ ከተማ፤ አደይ አበባ ስቴዲየም ተገኝተው አትሌቶቹን ማበረታታቸውም ተጠቅሷል።  ይህንኑም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፎቶ በታጀበ ዜና ይፋ አድርጓል ።

ከኢትዮጵያ ዜና ሳንወጣ፦ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ልምምዳቸውን መጀመራቸው ተጠቅሷል ። ቡድኑ ልምምዱን የጀመረው በፖላንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኬንያ ጋር ለሚኖረው ጨዋታ ነው ። ጥሪ ከተደረገላቸው 33 ተጫዋቾች መካከል ከተወሰኑት በስተቀር 26ቱ በልምምድ መገኘታቸው ተገልጧል ። በሴካፋ ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስመረጣቸው ተጨዋቾች በመጀመሪያው ቀን ልምምድ አልተገኙም የተቀሩት ግን ልምምዳቸውን አድርገዋል ተብሏል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በግብፅ አቻው 2 ለ0 በተሸነፈበት ግጥሚያ የስነምግባር ጥሰት በመፈጸሙ ለፊፋ ክስ ማቅረቡ ተገለጠ ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (FIFA) ቅሬታ ያቀረበው በሁለት ጉዳዮች ላይ ነው ። 1ኛ የግብፅ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የፍጹም ቅጣት ምት ባገኘበት ወቅት የግብጽ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ ዐይኖች ላይ ብርሃን ለቅቀዋል ይላል ።  2ኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር የአስተናጋጁ አገር ደጋፊዎች በፉጨት፤ በጩኸት እና በሌሎች ረባሽ ድምፆች በማወክ «የብሔራዊ መዝሙሩ» ክብር ባለመስጠት ከስሷል ። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የአፍሪቃ አገራት ዛሬ ውድድሮችን አካሂደዋል፤ ውድድሮች ነገም ይቀጥላሉ ። የነሐሴ 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የግብጽ ደጋፊዎች ላይ ለፊፋ ክስ አቀረበ

በዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ማጣሪያ ውድድር በመጥፎ ሁኔታ የጀመረው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አየርላንድ ላይ ድል ቀንቶታል ። ዘንድሮ ስድስት ጨዋታዎች የሚጠብቁት ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ብርቱ ፈተና ይጠብቀዋል ተብሏል ። የተጨዋቾች መጎዳት እና ቡድኑ በጊዜ ከፍተኛ ደረጃ አለመያዙ ሥጋት አጭሯል ። የጀርመን ቡድን ሐሙስ ዕለት በማጣሪያ ግጥሚያው ብራቲስላቫ ውስጥ ከስሎቫኪያ ጋር የ2 ለ0 አስደንጋጭ ሽንፈት ገጥሞታል ።

የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኮሎኝ ውስጥ ከሰሜን አየርላንድ ጋር ቅዳሜ ዕለት ሲጋጠምም ቡድኑ እና ደጋፊዎቹ በከፍተኛ ጭንቀት ተውጠው ነበር ምስል፦ Stuart Franklin/Getty Images

ኮሎኝ ውስጥ ከሰሜን አየርላንድ ጋር ቅዳሜ ዕለት ሲጋጠምም ቡድኑ እና ደጋፊዎቹ በከፍተኛ ጭንቀት ተውጠው ነበር ። በቅዳሜው ግጥሚያ ግን በርካታ የተጨዋቾች ለውጥ ያደረገው የጀርመን  ቡድን ሰሜን አየርላንድን 3 ለ1 ድል አድርጓል ። የቅዳሜው ድል ዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ለማለፍ ጊዜያዊ እፎይታ ነው ። በመቀጠል የሚኖሩ ጨዋታዎች ከወር በኋላ የሚከናወኑ ናቸው ። 

ካሜሩናዊው ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ከማንቸስተር ዩናይትድ ለመልቀቅ ሲስማማ ከአዲሱ ቡድኑ የሚያገኘው ደመወዝ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጠ ። በቱርኩ ትራቦዞንስፖር ቡድን ውስጥ የሚከፈለው ደመወዝ በኦልትራፎርድ ቆይታው በማንቸስተር ከሚያገኘው ወርኃዊ ደመወዝ እጥፍ መሆኑ ተዘግቧል ። የ29 ዓመቱ ግብ ጠባቂ፦ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2023 ማንቸስተር ዩናይትድን በ59 ሚሊዮን ዶላር ከተቀላቀለ በኋላ ለቡድኑ የሚጠበቅበትን ለማሳየት ሲንገታገት ቆይቷል ። የሐምሌ 28 ቀን 2017 ፤ የስፓርት ዘገባ

በሌላ ዜና የዝውውር ዜና፦ ማንቸስተር ሲቲ ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማን ከፈረንሳዩ ፓሪ ሳንጃርሞ አስፈርሟል ። የ26 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ለማንቸስተር ሲቲ 25 ቁጥር መለያ ለብሶ ይሰለፋል ተብሏል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW