1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጸሀይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ታየ

እሑድ፣ ሰኔ 14 2012

ዛሬ በአብዛኛው ኢትዮጵያ የታየው የፀሐይ ግርዶሽ በላሊበላ በርካታ የአገር ውስጥ ጎብኝዎች በተገኙበት በልዩ ሁኔታ ታይቷል፡፡ በስነስርዓቱ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናትና የዘርፉ ተመራማሪዎች መገኘታቸውን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Sonnenfinsternis 2020 | Indien Neu Delhi Bildkombo
ምስል፦ AFP/J. Samad

የጸሀይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ታየ

This browser does not support the audio element.

ዛሬ የተከሰተው የፀሐይ ግርዶሽ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መታየት ችሏል፡፡ በተለይ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በርካታ ህዝብ በተገኘበት ክስተቱ መታየቱን በስፍራው የተገኙ ተመልካቾች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

 በስፍራው ተገኝተው ክስተቱን ከተመለከቱት መካከል የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሁፎች ተመራማሪ መጋቢ አዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ እንደገለፁት በርካታ ህዝብ በቦታው ተገኝቶ ግርዶሹን እንደተመለከተና የራሳቸውን እይታም በስልክ ገልፀውልናል፡፡

የፀሐይ ግርዶሹ ላሊበላ ላይ ልዩ የሚያደርገውም ቅዱሳት ቤተክርስቲያናትን ነክቶ ስለሚሄድ እንደሆነ ነው ዶ/ር ሮዳስ ያብራሩት፡፡

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ቸኮለ ታዘበው ዛሬ የተከሰተውን የፀሐይ ግርዶስ ለመመልከት ተመራማሪዎችና የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በስፍራው ከተገኙ እንግዶች መካከል አስተያየታቸውን የሰጡን ግለሰብም የነበራቸውን ግምትና የተመለከቱትን ትዕይንት ለዶይቼ ቬለ እንዳስረዱት ድቅድቅ ጨለማ እንደሚሆን ገምተው የነበረ ቢሆንም ግርዶሹ ለእይታ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡

አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳዩን ከፈጣሪ ቁጣ ጋር ቢያያይዙትም በላሊበላ አካባቢ ግን ይህ ዓይነት አመለካከት እንደሌለ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቱ ኃላፊ ጸናግሯል፡፡

 የዚህ ዓይነት መጠነኛ ክስተት ከ18 ዓመት በኋላ በአገራችን አፋር አካባቢ እንደሚታይና ዛሬ የታየው ባለቀለበት ግርዶሽ ግን ከ146 ዓመት በኋላ ሊታይ እንደሚችል ተመራማሪው ዶ/ር ሮዳስ አመልክተዋል፡፡

 ዓለምነው መኮንን

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW