1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የፀጥታዉ ምክር ቤት ስብሰባ ስለ ሕዳሴዉ ግድብ

ዓርብ፣ ሐምሌ 2 2013

ምክር ቤቱ ትናንት ባደረገዉ ስብሰባ የሶስቱ ሐገራት ሚንስትሮች በየፊናቸዉ ያቀረቧቸዉን የልዩነት ምክንያቶች አድምጧል። የምክር ቤቱ አባል ሐገራት አምባሳደሮች ጉዳዩ በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት መፈታት አለበት የሚል ሐሳብ ሰንዝረዋል።

UN-Sicherheitsrat Sitzung
ምስል፦ Manuel Elias/UN/dpa/picture alliance

የሶስቱ ሐገራት ሚንስትሮች የልዩነታቸዉን ምክንያት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል

This browser does not support the audio element.

                 
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ሰበብ የገጠሙትን ዉዝግብ በመተማመን፣ በግልፅነትና በትብብር መንፈስ በመደራደር እንዲፈቱት አሳስበዋል። ምክር ቤቱ ትናንት ባደረገዉ ስብሰባ የሶስቱ ሐገራት ሚንስትሮች በየፊናቸዉ ያቀረቧቸዉን የልዩነት ምክንያቶች አድምጧል። የምክር ቤቱ አባል ሐገራት አምባሳደሮች ጉዳዩ በአፍሪቃ ሕብረት ሸምጋይነት መፈታት አለበት የሚል ሐሳብ ሰንዝረዋል።የምክር ቤቱን ስብሰባ በግብፅና በሱዳን ስም የጠራቸዉ ቱዚኒያ ነበረች። ቱኒዚያ ሶስቱ ሐገራት በአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበርና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አማካይነት እንዲደራደሩ፣ በስድስት ወራት ዉስጥም አሳሪ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚጠይቅ ረቂቅ ዉሳኔ አቅርባ ነበር። ሐሳቡ በምክር ቤቱ ተቀባይነት አላገኘም።

ታሪኩ ኃይሉ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW