1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮ የአዲስ አበባ ጉብኝት አንድምታ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 12 2017

ፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ በመንግስታቸው ድጋፍ ዕድሳት የተደረገለትን ብሄራዊ ቤተ መንግስት ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፈረንሳይ አብዛኛውን የምዕራብ አፍሪቃ ተደማችነቷን እና የጦር ሰፈሮቿን ካጣች በኋላ በምስራቅ አፍሪቃ የነበረውን ግንኙነቷን ለማጠናከር ያለመች መስሏል።

Frankreich Paris 2024 | Macron leitet Krisensitzung zu Folgen des Zyklons Chido auf Mayotte
ምስል Ludovic Marin/REUTERS

የፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአዲስ አበባ ጉብኝት እና አንድምታው

This browser does not support the audio element.

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ በመንግስታቸው ድጋፍ ዕድሳት የተደረገለትን ብሄራዊ ቤተ መንግስት ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፈረንሳይ አብዛኛውን የምዕራብ አፍሪቃ ተደማችነቷን እና የጦር ሰፈሮቿን ካጣች በኋላ በምስራቅ አፍሪቃ የነበረውን ግንኙነቷን ለማጠናከር ያለመች መስሏል።

የአውሮጳ ባለሥልጣናት የኢትዮያ ጉዞ አንደምታ

ማክሮን ወደ አዲስ አበባ ከማቅናታቸው በፊት በጂቡቲ የሚገኘውን የፈረንሳይ የጦር ሰፈር የጎበኙ ሲሆን ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ጊሌ ጋርም ተነጋግረዋል። ማክሮን ከአምስት ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ሀገራቸው በኢትዮጵያ በተለይ በቅርስ  ጥበቃ ረገድ ያደረገችውን ድጋፍ ይመለከታሉ ተብሏል። በመዲናዋ አዲስ አበባም ከቤተመንግስት በተጨማሪ ሌሎች አካባቢዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

ኃይማኖት ጥሩነህ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW