የፈረንሳይ ሁከት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 27 2015
ማስታወቂያ
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ ሐገራቸዉን ያመሰቃቀለዉ ሕዝባዊ ቁጣና ተቃዉሞን መሠረታዊ ምክንያት ለማጥናት ከባለስልጣኖቻቸዉን ጋር ዛሬ ተነጋግረዋል።አንድ የ17 ዓመት ወጣት በፖሊስ ጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ሰበብ የተቀጣጠለዉ ቁጣ በመላዉ ፈረንሳይ ከፍተኛ ትርምስ አስከትሏል።አመፅና ተቃዉሞዉ ከትናንት ማታ ጀምሮ ጋብ ቢልም በነጭ ፈረንሳዎችና ሌላ ቀለም ባላቸዉ የሐገሪቱ ዜጎች መካካል የፈጠረዉ ልዩነት ግን አሁንም እንደተካረረ ነዉ።ለገዳይ ፖሊስ ቤተሰቦች መርጃ ከ1.4 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ሲዋጣ፣ የሰሜን አፍሪቃ ዝርያ ላላቸዉ የሟች ቤተሰቦች የተዋጣዉ ግን ከ350 ሺሕ ዩሮ ያነሰ ነዉ።
ኃይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ