1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፊቼ ጫምበላላ በዓል በሀዋሳ ተከብሮ ዋለ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 28 2016

ዛሬ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምበላላ በዓል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ መሰብሰቢያ ሥፍራ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል ፡፡ በበዓሉ ላይ በሀዋሳ ከተማ እና ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የመጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ታድመዋል ፡፡

Äthiopien Neujahrsfest der Sidama
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ፊቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ እየተከበረ ነው

This browser does not support the audio element.

ዛሬ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምበላላ በዓል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ መሰብሰቢያ ሥፍራ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል ፡፡ በበዓሉ ላይ በሀዋሳ ከተማ እና ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የመጡ በሺህዎች  የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ታድመዋል ፡፡

አዲስ ዓመትን በይቅርታ በሲዳማ ክልል

ዶቼ ቬለ  አስተያየታቸውን  ከጠየቃቸው የበዓሉ ታዳሚች መካከል  ኤርሚያስ ግርማ እና እቴነሽ ላሌሞ በዓሉን በናፍቆት ሲጠበቁት መቆየታቸው ተናግረዋል ፡፡ ለዋናው በዓል ሰፊ ዝግጅት ሲያድርጉ መቆየታቸውን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ አሁን ላይ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን እያከበሩት እንደሚገኙ ገልጸዋል ፡፡   

ዶቼ ቬለ  አስተያየታቸውን  ከጠየቃቸው የበዓሉ ታዳሚች መካከል  ኤርሚያስ ግርማ እና እቴነሽ ላሌሞ በዓሉን በናፍቆት ሲጠበቁት መቆየታቸው ተናግረዋል ፡፡ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በበዓሉ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ፊቼ ጨምበላላ ሰዎች ከአምላክም ሆነ ከሰው ጋር ይቅር የሚባባሉበት  ሥርዓት ነው ብለዋል ፡፡ በዓሉ መለያየትና መራራቅ የሚወገዝበት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ “ ፊቼ ለሰው ልጆች በሙሉ  የሚጠቅመውን ሰላም ለማረጋገጥ ሁነኛ ባህላዊ እሴት ነው “ ብለዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት ሌላው የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ በበኩላቸው ፊቼ ጫምበላላ ታሪካዊና ባህላዊ እሴቱ ተጠብቆ ወደ ቀጣዩ ትውልድ እንዲሸጋገር ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW