1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፌደራል ስርዓቱ ሊሻሻል ይገባል ተባለ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 10 2011

የኢትዮጵያ የፌዴራላዊ ስርአት ብሄር ተኮር ይሁን ወይንስ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥን ይከተል በሚለው ዙሪያ ውይይት እና ክርክር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ላይ አሁን ያለው የፌዴራል ስርአት አወቃቀር ሙሉ በሙሉ ሃገሪቱ ለገባችበት ቀውስ ምክንያት ባይሆንም የጎላ ችግር ነበረው የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

Äthiopien | Debatte über das äthiopische föderalistische System
ምስል DW/S. Muchie

የፌደራል ስርዓቱ ሊሻሻል ይገባል ተባለ

This browser does not support the audio element.

አሁን ያለው የፌደራላዊ መንግስት አወቃቀር ስርአት ጊዜውን እና የተለወጡ በርካታ ማህበረ ፖለቲካ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን ማስተናገድ የማይችል በመሆኑ ሊሻሻል ይገባል የሚል ምክረ ሃሳብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተሰንዝሯል። ከተወያዮቹ መካከል የተለየ ሃሳብና አማራጭ ነው ያሉትን ሃሳብ የዘረዘሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ዋናው ስርአት ፌዴራላዊ ሆኖ ነገር ግን ከአሃዳዊ ስርአት በጎ አካሄዶችንም መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል። 

አቶ ልደቱ በቀበሌ እና ወረዳ ደረጃዎች ላይ አሁን ያለው ብሄር ተኮር አወቃቀር መቀጠል አለበት ባይ ናቸው። ሆኖም በማዘጋጃ ቤት ደረጃ መደራጀት የሚችል ህዝብ ቁጥር ያላቸው ከተሞች ላይ አሃዳዊ ስርአት ሊዘረጋ እንደሚገባ አማራጭ ያሉትን አቅርበዋል። በዞን እና በክልል ደረጃ መስፈርቱ ከቋንቋ እና ማንነት በላይ ያሉ ጉዳዮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት የሚል ሃሳብም ሰንዝረዋል። 

ምስል DW/S. Muchie

በውይይቱ ላይ ሃገራዊ አንድነትን እና የአናሳዎችን መብት ማስከበር የሚችል፣ ሁሉም የሚሳተፍበት ኢትዮጵያን እንደኢትዮጵያ ማስቀጠል የሚችል ፌዴራላዊ ስርአት ሊዋቀር ይገባል የሚል ሃሳብ ተንጸባርቋል። የፌደራላዊ ስርዓቱ አሁን በሀገሪቱ ለሚታየው ችግር አስተዋጽኦ እንዳለው የጠቀሱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከህገመንግስት ጀምሮ ማሻሻያ እንዲደረግበት አሳስበዋል። የትኛው ስርዓት ይሻላል በሚለው ላይ ሁሉም ሊወያይበት ይገባልም ተብሏል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ሰለሞን ሙጬ

ተስፋለም ወልደየስ

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW