1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ስለ አክሱም

ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2013

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ «ሕወሃት» እና «ሸኔ» በሽብር ስለተፈረጁበት እንዲሁም በአክሱም ከተማ ስለተፈጸመው የሰብአዊ ቀውስ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ። የኢፌዴሪ ሠራዊት ለሌላ ግዳጅ ሕዳር 18 ቀን፣ 2013 ዓ.ም አክሱም ከተማን ለቅቆ እንደወጣ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ከተማዋ መግባቱና ከሕወሓት ጋር ውጊያ 93 ሰዎች መሞታቸውን ገልጧል።

Äthiopien Fikadu Tsega
ምስል Solomon Muchie/DW

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማብራሪያ ሰጥቷል

This browser does not support the audio element.

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ «ሕወሃት» እና «ሸኔ» በሽብር ስለተፈረጁበት እንዲሁም በአክሱም ከተማ ስለተፈጸመው የሰብአዊ ቀውስ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ። የኢፌዴሪ ሠራዊት ለሌላ ግዳጅ ሕዳር 18 ቀን፣ 2013 ዓ.ም አክሱም ከተማን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ከተማዋ መግባቱና ከሕወሓት  ጋር በነበረ ጦርነት ንፁሃንን ጨምሮ የደንብ ልብስ ያልለበሱ ግን በአብዛኛው በጦርነቱ የተሳተፉ የ93 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ገልጿል። የኢፌዴሪ ሠራዊት አክሱም በነበረበት ወቅት የተተኮሰ መድፍ ዒላማውን ስቶ በመኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ አምስት ሰዎች እንዲሁም ከሰዓት እላፊ ጋር በተገናኘ አንድ በድምሩ ስድስት ሰዎች በኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን ባወጣው የምርመራ ውጤት ይፋ አድርጓል። በሌላ በኩል 116 ሴቶች የአስገድዶ መደፈር ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ለፖሊስ ቃላቸውን መስጠታቸው ተገልጿል። በወንጀሉ የተሳተፉ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳያቸው በክልሉ ዐቃቤ ሕግ እና በወታደራዊ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተላልፈው ተሰጥተዋል ተብላል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW