1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍልሥጤማውያን በተመድ የታዛቢነት ዕውቅና ማግኘት

ዓርብ፣ ኅዳር 21 2005

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የፍልስጤም ራስ ገዝ መስተዳድር በዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ሙሉ ታዛቢነት መቀመጫ እንዲኖረዉ ያቀረበዉን ጥያቄ በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ አፀደቀ። ትናንት በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ

GettyImages 157171574 Palestinians celebrate in the West Bank city of Ramallah on November 29, 2012 after the General Assembly voted to recognise Palestine as a non-member state. The UN General Assembly on Thursday voted overwhelmingly to recognize Palestine as a non-member state, giving a major diplomatic triumph to president Mahmud Abbas despite fierce opposition from the United States and Israel. AFP PHOTO / ABBAS MOMANI (Photo credit should read ABBAS MOMANI/AFP/Getty Images)
ምስል AFP/Getty Images

ሥርዓት ከ 193 የተመድ አባል ሀገራት መካከል 138 የፍልሥጤማውያን ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ ያቀረቡትን ማመልከቻ ሲደግፉ ዘጠኝ ተቃውመውታል፤ 41 ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። ድምጽ ከመስጠት ከተቆጠቡት መካከል ጀርመን አንዷ ስትሆን፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከደገፉት ሀገራት መካከል ናቸው። ፍልሥጤማውያን አሁን በተመድ የያዙት የታዛቢነት አቋማቸው በድርጅቱ ውስጥ ይዘውት የነበረውን ብቸኛውን የመናገር መብት በማሻሻል ወደፊት በድርጅቱ በሚካሄዱ ክርክሮች በጠቅላላ እንዲሳተፉ፡ እንዲሁም፡ በተለያዩት የተመድ አካላት ውስጥ በአባልነት እንዲገቡ ያስችላቸዋል። እስከትናንቱ ውሳኔ ድረስ በተመድ ውስጥ የታዛቢነት አቋም የያዘችው የድርጅቱ አባል ያልሆነችው ቫቲካን ብቻ ነበረች። በራማላህ እና በጋዛ ሲቲ በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የ,ተካሄደውን የድምፅ አሰጣጡን በትላልቅ ቴሌቪዥኖች የተከታተለው የፍልሥጤም ሕዝብ በውሳኔው መደሰቱን ገልጾዋል። በመላው ዓለም የሚገኙት ፍልሥጤማውያን ውሳኔውን ትልቅ ትርጓሜ የያዘና ሀገር ወደመሆን ደረጃ የሚያሸጋግር የመጀመሪያው ርምጃ አድርገው ተመልክተውታል። ዩኤስ አሜሪካ እና እሥራኤል የትናንቱን ውሳኔ በፍልሥጤማውያን እና በእእሥራኤል መካከል ዘላቂ ሰላም የማያመጣ ነው በሚል ተቃውመውታል።

ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ በተመድምስል picture alliance / dpa
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW