1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍራንኮ ቫሎታ መገታት፡ ገበያውን ለማረጋጋት ወይስ ትይዩ የውጪ ምንዛሪን ለመቆጣጠር?

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 30 2017

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘይትን ጨምሮ የተወሰኑ መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ከየትም ምንጭ በሚገኝ የውጪ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሎታ) ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ሲፈቅድ የውጪ ምንዛሪውን እጥረት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ገቢያውን ለማረጋጋት ነበር፡፡

Symbolbild | Frachtcontainer mit äthiopischer Nationalflagge
ምስል Everyonephoto/Pond5 Images/IMAGO

በኢትዮጵያ የፍራንኮ ቫሎታ መታገድ እና አንድምታው

This browser does not support the audio element.

የፍራንኮ ቫሎታ መገታት፡ ገበያውን ለማረጋጋት ወይስ ትይዩ የውጪ ምንዛሪን ለመቆጣጠር?

የኢትዮጵያ መንግስት በሃምሌ ወር መጨረሻ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ካደረገ ወዲህ በትናንትናው እለት የትኛውም አይነት ምርት በፍራንኮ ቫሎታ ስርኣት ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡

 

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘይትን ጨምሮ የተወሰኑ መሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ከየትም ምንጭ በሚገኝ የውጪ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሎታ) ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ሲፈቅድ የውጪ ምንዛሪውን እጥረት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ገበያውን ለማረጋጋት ነበር፡፡

መንግስት ትናንት ውሳኔውን ሲያሳወቅ አሁን ላይ በባንኮች የሚገኝ የውጪ ምንዛሪ በቂ መሆኑን በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ግን ውጥኑ በዋናነት የትይዩ ገቢያ (ጥቁር ገቢያ) ተፈላጊነትን ለመቀነስ ሊሆን እንደምችልም ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ንግስት ትናንት ውሳኔውን ሲያሳወቅ አሁን ላይ በባንኮች የሚገኝ የውጪ ምንዛሪ በቂ መሆኑን በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡ምስል Solomon Muchie/DW

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው ዓለሙ አስተያየጣውን የጀመሩት የፍራንኮ ቫሎታ ምንነትና አስፈላጊ የሚሆንበትን ወቅት በማብራራት ነው፡፡ “አገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ገጥሟት በአገሪቱ ባንክ ስወርዓት ስር ብቻ በሚያልፍ መልኩ ምርቶችን ከውጪ ማስገባት አዳጋች ሲሆን የሚፈቀድ ወይም እንደ አማራጭ የሚቀርብ ስርዓት ነው ፍራንኮ ቫሎታ፡፡ ይህ የሚሆነው ከየትም በሚገኝ የውጪ ምንዛሪ የተወሰኑትን ምርቶች (በብዛት በገቢያ የሚፈለጉና አንገብጋቢ የሆኑትን) ወደ አገር በሚገቡበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ስርዓት ባንኮች ያለባቸውን የውጪ ምንዛሪ እጥረት እስኪወጡ ሊፈቀድ የሚችልም ነው” ብለዋል፡፡

የፍራንኮ ቫሉታ መፈቀድ ጥቅሙና የጎንዮሽ ጉዳቱ

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴርም በትናትናው እለት ለታዘዙት ምርቶች ከተሰጠው የሁለት ሳምንት ጊዜ ውጪ፤ በፍራንኮ ቫሎታ የሚገቡ ምርቶች ከትናንት ጀምሮ እንዲገቱ ስወስን በባንኮች በቂ የውጪ ምንዛሪ መኖሩን በምክንያትነት በማቅረብ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ፍራንኮ ቫሎታ በኢኮኖሚ ሽግግር ወቅት የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችን ዋጋ ለማረጋጋት የነበረውን አስተዋጽኦም አልሸሸገም፡፡ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ ባለሙያው አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን ደግሞ ትርጉሙ ከዚህም ልልቅ ይችላል ነው የሚሉት፡፡ “ትርጉሙ በተወሰነ መልኩም ቢሆን በመንግስት በኩል ኢኮኖሚው ተረጋግቷል የሚል አንድምታ በመኖሩ ተወስኖ ሊሆን እንደሚችልም ነው የተመላከተው፡፡ የውጪ ምንዛሪ አቅርቦቱ ከኢኮኖሚው ማሻሻው ወዲህ በገቢያ መወሰኑ ችግሮቹን አቃሎልኛል የሚል አንድምታም በዚህ ውስጥ ይታያል” ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴርም በትናትናው እለት ለታዘዙት ምርቶች ከተሰጠው የሁለት ሳምንት ጊዜ ውጪ፤ በፍራንኮ ቫሎታ የሚገቡ ምርቶች ከትናንት ጀምሮ እንዲገቱ ስወስን በባንኮች በቂ የውጪ ምንዛሪ መኖሩን በምክንያትነት በማቅረብ ነው፡፡ምስል Eshete Bekele/DW

 

ይሁንና ይላሉ አቶ ሸዋፈራሁ፡፡ መሰል ውሳኔዎች ላይ የሚያደርስ የኢኮኖሚው መረጋጋት በተለይም በሸማች በኩል ጊዜው የደረሰ አይመስልም፡፡ “እኔ እንደማየው የተቸኮሌ ይመስለኝል፡፡ ውሳኔው ሃብታምን የበለጠ ሃብታም ደሃውንም የበለጠ ደሃ ሊያደርግ ይችላል፡፡ መሰል ውሳኔን ለማሳለፍ ለአብነት መንግስት የውጪ ምንዛሪ ከፍ ብሎ የሚወስድም ጠፋ በሚልበት ባሁን ወቅት ተገቢ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ግን ደግሞ የኑሮ ሁኔታ በተለይም ገቢያው መረጋጋትን አሳይቷል ወይ ብባል የማህበረሰቡ ምላሽ ያንን የሚያሳይ አይመስልም” በማለት በወቅታዊነቱ ላይ በምክከታቸው ጥያቄን አንስተዋል፡፡

ሕገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው ዓለሙ በፊናቸው ለውሳኔው ሌላውም መላምታውንም ስገልጹ፤ የፍራንኮ ቫሎታ እንዲቆም መወሰን የትይዩ ገቢያን ፍላጎት ልገታ እንደምችል ጠቁመዋል፡፡ “ፍራንኮ ቫሎታ ካለ ሰዎች የውጪ ምንዛሪን ከትይዩ ገቢያ እየገዙ በዚያ ምርት ያስገባሉ የሚል ኢኮኖሚያዊ ግምት አለ፡፡ ምናልባት አሁን የፍራንኮ ቫሎታ መቆም በትይዩ ገቢያው ላይ የሚታየውን ፍላጎት በእጅጉ ሊቀንስ ስለሚችል ውሳኔው ለዚህም የተላለፈ ሊሆን ይችላል” ሲል አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ቀርበው ንግግር ስያደርጉ የፍራንኮ ቫሎታን አሉታዊነት አንስተው ልቆም ሚችልበት አግባብ ላይ መንግስታው እያጠነ መሆኑን ፍንጭ መስጠታቸውም ይታወሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW