1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍትህ ተቋማት ማሻሽያ በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ መጋቢት 15 2008

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የኢትዮጲያ ፍትህ ሚኒስቴርን አፍርሶ በምትኩ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ተቋም ለመመስረት ረቅቅ አዋጅ ለምክር ቤት መቅረቡ ተሰምቷል።

Äthiopien Parlament Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G. Egziabher

[No title]

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጲያ ፍትህ ሚንስቴርን አፍርሶ በምትኩ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ተቋም ለመመስረት ረቅቅ አዋጅ ለሐገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ነበር እ። ይህንንም ተከትሎ ምክር ቤቱ <<ለዝርዝር እይታ>> ለሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንደተመራና ዉሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተዘግበዋል። የፍትህ ምንስቴሩን ማፍረስ እና አዲሱን የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ማቋቋም የተፈለገበት ምክንያት አስመልክቶ መርጋ ዮናስ የሚከተለ ዘገባ አጠናቅሯል።

ለምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራው ይኽው ረቂቅ አዋጅ ከፀደቀ የፍትህ ሚኒስቴር እንደሚፈርስ ሬፖርተር የተሰኘዉ ጋዜጣ ዘግቧል።

ጋዜጣው ይህንኑ ጉዳይ የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ አምባዬ ማረጋገጣቸውን ጠቅሷል ።በፍትህ ሚንስቴር የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ፋንታሁን አንባዉ ግን ፍትህ ሚኒስቴር ይፈረሳል ስለ መባሉ መረጃ እንዴሌላቸዉ፣ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደሚቋቋም ግን እንደሚያውቁ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

አሁን በአዋጅ ደረጃ ስላለው ጉዳይ አሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም ሃላፊነት ዝርዝር መረጃ መስጠት እንደሚያስቸግር አቶ ፋንታሁን ይናገራሉ።ይህ ለዉጥ በመደረጉ በአገሪቱ የፍትህ ስርዓት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል ወይ ? ብለን በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ደህረ ገፅ ላይ ዉይይት አካሄዴን ነበር።

የአቃቤህግ ሥራ በተለያዩ ተቋማት ተበትኖ በመሆኑ ጉዳዬች እንደምጓተቱ እና ባለጉዳዮችም ጉዳያቸውን የት ማቅረብ እንዳለባቸው ባለማውቅ እንደሚጉላሉ ይናገራሉ። ስላዚህ ባንድ ተቋም ስር መሆኑ ይህን ችግር ሊቀርፍ ይችላል ፣ የተሻለ ተቋማዊ ነፃነትም ሊኖረው ይችላል ስሉ አስተያየተቸዉን ሰጥተውናል።

አብዛኛዉ ተወያይ ግን<<ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም>> በማለት ኢትዮጲያ ዉስጥ ለፍትህ ስርዓቱ በነፃነትና ገለልተኝነት እንደማያሰራ ተችተዋል። የተቋም ስም ከመለዋወጥ ባሻገር አገሪቱ ዉስጥ ስር ነቀል የፍትህ ስርዓት ያስፈልጋል ሲሊም አስተያየታቸውን አስፍረዋል።

ምስል DW/G. Tedla HG

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW