1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍኖተ ሰላም የቡሬ እና የሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች የዛሬ ውሎ

ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2015

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደብረ ብርሀን ፣በፍኖተ ሰላም እና በቡሬ ከተሞች በተካሄደ ውጊያ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ታማኝ ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በዚሁ መግለጫ ከሚሽኑ በመኖሪያ አካባቢዎችና የሕዝብ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች እንደደረሱት ገልጿል።

የፍኖተ ሰላም ከተማ
በደብረ ብርሀን፣ ፍኖተ ሰላም እና ቡሬ ከተሞች በተፈጸሙ ጥቃቶች እና የከባድ መሣሪያ ድብደባዎች በርካታ ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ የመኖሪያ አካባቢዎች እና የሕዝብ ተቋማት መጎዳታቸውን የሚጠቁሙ ተዓማኒ ሪፖርቶች እንደደረሰው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል።ምስል Privat/Addis standard

የፍኖተ ሰላም ፣የቡሬና የሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ይዞታ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደብረ ብርሀን ፣በፍኖተ ሰላምና በቡሬ ከተሞች በተካሄደ ውጊያ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ ታማኝ ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በዚሁ መግለጫ ከሚሽኑ በመኖሪያ አካባቢዎችና የሕዝብ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች እንደደረሱት ገልጿል።

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ከባድ መሣሪያ ጭምር ጥቅም ላይ በዋለባቸው ውጊያዎች ሰዎች መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውን እና ንብረት መውደሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። "መንገዶችን ለመዝጋት የሞከሩ ሲቪሎችን ጨምሮ ተቃዋሚዎች የተገደሉባቸው አጋጣሚዎች" መኖራቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እስር ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች መሰበራቸውን፤ የጦር መሣሪያዎች እና ጥይቶች መዘረፋቸውን አትቷል። ከማረሚያ ቤቶች የቅድመ ፍርድ እስረኞች እና ታራሚዎች እንዳመለጡም መግለጫው ይጠቁማል

የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ

በደብረ ብርሀን ከተማ ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው አራት ቀበሌዎች ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን 2015 በተደረጉ ከባድ ውጊያዎች ሲቪሎች በሆስፒታሎች፣ በቤተ-ክርስቲያን፣ በትምህርት ቤት እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው እና በሥራ ቦታዎች እያሉ በከባድ መሣሪያ ፍንጣሪዎች ወይም በተባራሪ ጥይት እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። በደብረ ብርሀን፣ ፍኖተ ሰላም እና ቡሬ ከተሞች በተፈጸሙ ጥቃቶች እና የከባድ መሣሪያ ድብደባዎች በርካታ ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ የመኖሪያ አካባቢዎች እና የሕዝብ ተቋማት መጎዳታቸውን የሚጠቁሙ ተዓማኒ ሪፖርቶች እንደደረሰው ኮሚሽኑ ገልጿል።

በደብረ ብርሀን ከተማ ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው አራት ቀበሌዎች ሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን 2015 በተደረጉ ከባድ ውጊያዎች ሲቪሎች በሆስፒታሎች፣ በቤተ-ክርስቲያን፣ በትምህርት ቤት እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው እና በሥራ ቦታዎች እያሉ በከባድ መሣሪያ ፍንጣሪዎች ወይም በተባራሪ ጥይት እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ምስል Eshete Bekele/DW

በባሕር ዳር ከተማ በርካታ አካባቢዎች ሲቪል ሰዎች በጎዳናዎች ወይም ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ መገደላቸውን የጠቆመው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን "በተለይ አንዳንድ ወጣቶች ለፍተሻ ኢላማ ተደርገዋል፤ ድብደባ እና ግድያ ተፈጽሞባቸዋል" ብሏል። በተለያዩ የጎንደር ከተማ አካባቢዎች የሲቪሎች ግድያ እና የንብረት ውድመት፤ በሸዋሮቢት በጸጥታ አስከባሪዎች የዘፈቀደ ግድያ መፈጸሙን የሚጠቁሙ ተዓማኒ ሪፖርቶች እንደደረሰውም አስታውቋል።

በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዚህም ሳቢያ በብዙ ቦታዎች አካባቢያዊ የመንግሥት መዋቅሮች ጊዜያዊ መፍረስ እንዳጋጠማቸው እና የመንግሥት ባለሥልጣናት መገደላቸውን አስታውቋል።

የአማራ ክልል ከተሞች የሰዓት ዕላፊ ገደብና የዕለቱ እንቅስቃሴ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዛሬው ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ የአማራ ብሔር አባላት እና ኤርትራውያን ስደተኞች ከፍተኛ እስር እንደተፈጸመ አስታውቋል። ከታሳሪዎች ቤተሰቦች እና ጓደኞች በርካታ ሪፖርቶች እንደደረሰው የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ነገር ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገበት ጊዜ ጀምሮ የእስር ሁኔታዎችን ለመከታተል ፈቃድ እንዳላገኘ ገልጿል።  መንግሥት እስሩን እንዲያቆም፤ በዘፈቀደ የታሰሩትንም እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል።

በመግለጫው መሠረት የኤሌክትሪክ፣ ውኃ፣ ባንክ፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ስልክ እና ኢንተርኔትን ጨምሮ መሠረዊ አገልግሎቶች በበርካታ አካባቢዎች ተቋርጠዋል። የንግድ መደብሮች መዘጋታቸውን የገለጸው ኮሚሽኑ የክልሉ ነዋሪዎች በውጊያው ምክንያት የለት ተለት ሥራቸውን መከወን ተከልክለው በቤታቸው ለመቀመጥ እንደተገደዱ ገልጿል።

ትናንት የአየር ጥቃት የተፈጸመበት የፍኖተ ሰላም ከተማ ውጊያ ይካሄድበት ነበር የተባለው የቡሬ እንዲሁም የሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ይዞታ ምን እንደሚመስል የባህርዳሩን ወኪላችንን አለምነው መኮንን በስልክ ነግሮናል።

አለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW