1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር በአሶሳ

ዓርብ፣ ኅዳር 28 2016

በአሶሳ ከተማ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች እንደገለፁት በተለይ ጤፍ፣ሽንኩርት፣ቡና እና ሌሎች ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ ነው፡፡ ፡፡ የክልሉ ንግድና የገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ገብረ ሀይል በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

አሶሳ ከተማ በከፊል
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የአሶሳ ከተማ ገፅታ በከፊል ምስል Negassa Dessalegen/DW

የሸቀጦች ዋጋ ማሻቀብ በአሶሳ

This browser does not support the audio element.

በአሶሳ ከተማ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የጤፍ፣የሽንኩርት፣ቡና እና ሌሎችም ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት አንድ ኪ.ሎ ሽንኩርት 180 ብር ገብቶ የነበር ሲሆን አሁን ከሰኞ ጀምሮ ደግሞ በ150 ብር መግዛታቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ የጤፍም ዋጋ በኪሎ ከ110 ብር እስከ 115 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ተገልጸዋል፡፡ የክልሉ ንግድና የገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ገብረ ሀይል በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ከአጎራባች ክልሎች አልፎ አልፎ በሚከሰተው የመንገድ መዘጋት ምክንያት ምርት እየገባ እንዳልሆነም ተገልጸዋል፡፡
የምርት ዋጋ መጨመር መንስኤዎች
በአሶሳ እና አካባቢ የፍጆታ ምርትና ሌሎችም በየጊዜው እየጨመረ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኑሮ ፈታኝ እያደረገ እንደሚገኝ ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ አንድ ኩንታል የጤፍ ዋጋ ከ10ሺ እስከ 11ሺ 500 ብር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው የምመረተው የሽንኩርት ዋጋ በኪሎ ከ140 እስከ 160 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ከመማሪያ ደብተር አንስቶ በሁሉም ቁሳቁስና ምርት ላይየዋጋ ጭማሪ መደረጉንም ነዋሪዎቹ አንስተዋል፡፡በአካባቢው የሚመረቱ እንደ ሽንኩረትና ቲማቲም ያሉ ምርቶች ዋጋ መሻሻል እንዳለበት ነዋሪዎቹ ጠቁሟል፡፡ በተደጋጋሚ መንገድ ተዘግቷል በሚል ሰበብ በየዕለቱ የዋጋ ጭማሪ እንደሚደረግ ገልጸው በከተማው የሚስዋለውን ዋጋ ጭማሪ በመንግስት በኩል ዘለቂ በሆነ መልኩ ማስተካከያ እንዲደረግና በቂ ምርት ከአጎራባች ክልሎች በእጀባ እንዲገባ ነዋሪዎች ሀሳብ አቅርቧል፡፡

የአሶሳ ከተማ ገፅታ በከፊልምስል Negassa Dessalegen/DW

የመንገድ መዘጋትና የአቅርቦት ችግር
በአሶሳ ከተማ እና አካባቢው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመከላልና ለመቆጣጠር ሲባል ግብረ ሀይል ተቋቁሙ ወደ ስራ ከገባ ወራት እንደስቆጠረም የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገልጸዋል፡፡ በቅርቡ 15 የሚደርሱ በንግድ ላይ የተሰማሩና ምክንያታዊ ያልነሆ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጀሊ ሙሳ ለዶቸቨሌ ተናግረዋል፡፡

አቶ አጀሊ ሙሳ፤ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጀሊ ሙሳምስል Negassa Dessalegn/DW

ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ ምርቶች ዋጋ በትራንስፖርትና መንገድ መዘጋጋት ምክንያት የምርቶች ዋጋ እንደሚጨምር የክልሉ መንግስት አመልክቷል፡፡

ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡ ምርቶች በሁለቱም አቅጣጫዎች በበቂ ሁኔታ ምርት እየገባ እንዳልሆነም አቶ አጀሊ ሙሳ ጠቁሟል፡፡ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር ለተቋቋመ ግብረ ሀይል ጥቆማዎች እንዲሰጡ ቢገለጽም ከተጠቃሚዎችም ጥቆማ በብዛት እየመጣ አይደለም ብሏል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ ከዚህ ቀደም ለአምስት ወራት የሚቆይ የኑሮ ውድነት ቅነሳ መርሀ ግብር ተግባራዊ ተገደርጓል፡፡ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ እና ዋጋ ለመጨመር ሲባል ምርት በሚያከማቹ ግለሰቦች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች ለመውሰድ ሲባል ከመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ግብር ሀይል ተቋቁሞ በስራ ላይ እንደሚገኝም የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ነጋሳ ደሳለኝ

ፀሐይ ጫኔ

አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW