1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት መሪዎች ስለ ጋዛ ሰላማዊ ሰዎች እልቂት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 27 2016

ሀማስ በእስራኤል ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ፈጥነው የተቃወሙትና ያወገዙት አውሮፓውያን፤ እስራኤ በጋዛ በከፍተቸው ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች የሚደርሰውን ሞትና መፈናቀል በበቂ ሁኒታ አላወገዙም በሚል በብዛት እይተተቹና በርካቶችም አደባባይ በመውጣት ጭምር እያወገዟቸው ነው።

የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላይን ፎቶ
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላይን ፎቶምስል Dursun Aydemir/Anadolu/picture alliance

የአዉሮጳ ሕብረት ባለስልጣናት በጋዛ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን «አሳዛኝ»አሉት

This browser does not support the audio element.

በአውሮፓ ህብረት፤ አሜሪክና እስራኤል በአሸባሪነት የተፈረጀው ሀማስ ልክ የዛሬ ወር  በእስራኤላውያን  ላይ ባደረሰው ጥቃት ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደሉን ተክትሎ፤ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የከፈተችው ጦርነት ላፍታ እንዲቆምና የሰብአዊ እርድታ ማስተላለፊያ ኮሪደር እንዲከፈት  በአውሮፓ ህብረትና የመንግሥታቱ ድርጅት ጭምር የቀረበው ጥሪ እስካሁን ተቀባይነት አላገኘም፡፤ በጋዛላይ የሚካሄደው የአየር ድበደባ በስደተኛ ካምፖች ሳይቀር እንደደረሰ የተገለጸ ሲሆን፤ ጦርነቱ በምድርም ጭምር እንደቀጦለና እስክሁንም ከአስር ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉና እንደሞቱ መረጃዎች ያሳያሉ።

ሀማስ በእስራኤል ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ፈጥነው የተቃወሙትና ያወገዙት አውሮፓውያን፤ እስራኤ በጋዛ  በከፍተቸው ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች የሚደርሰውን ሞትና መፈናቀል በበቂ ሁኒታ አላወገዙም በሚል በብዛት እይተተቹና በርካቶችም አደባባይ በመውጣት ጭምር እያወገዟቸው ነው። ለትችት ክተጋለጡት የህብረቱ ባለስልጣኖች  ውስጥ አንዷ የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቮንዴረለየን ሲሆኑ፤ እሳቸውም የሃማስን ጥቃት ተክትሎ ቴላቪቭ ድረስ በመሄድ ለእስራኤል  ድጋፍቸውን ሲገልጹ፤ በጋዛ  እይተፈጸመ ስላለው ውድመትና የስላማዊ ሰዎች እልቂት በወቅቱ ምንም ሳይሉ በመቅረታቸው ነበር የተወቀሱትና ሲተቹ የከረሙት ።

እናትና ልጅ-ከጥቃት ሽሽት ጋዛምስል Belal Khaled/AA/picture alliance

ከትናንት ሰኞ  ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች ጉባኤ ላይ ባደጉት ንግግር ግን፤  ወይዘሮ ቮንዴር ሌየን፤ በእስራኤል የተፈጸመውን ጥቃት ማውገዝና ከእስራኤል ጎን መቆም ተገቢ ቢሆንም፤  ከዚህ እኩል  በጋዛ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት የሚያሳዝናቸው  መሆኑን በግልጽ ቋንቋ ገልጸዋል፤” ክህንጻ ፍርስራሾች የሚወጡት ህጻናት ምስል ልብን በህዘን የሚያደማ ነው” በማለትም  ሁላችንም ዲሞክራቶችና ሰዎች የሆን ሁሉ በእንደዚህ አይነት ስቃይና ግፍ ያሉ ሰዎችን መርዳትና  መታደግ ያስፈልገናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሚሽኑ  በአሁኑ ወቅት በሰባዊ እርዳታ፣ የታጋቾች ጉዳይና ጦርነቱ እንዳያድግና እንዳይዛመት  ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑን  የገለጹት ወይዘሮ ቮንዴረልየን፤ ለጋዛ ሰባዊ እርድታ ተጨማሪ 25 ሚሊዮን  ኢሮ የተለገሰ መሆንና  ይህም የኮሚሽኑን የዚህ አመት የሰባዊ እርድታ አስተዋጾ አንድ መቶ ሚሊዮን ኢሮ እንደሚያደርሰው  አስታውቀዋል:

ወይዘሮ ቮንዴርሌየን ከግዚያዊው ችግርና እርዳታ በዘለል ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ መሻትና መስራት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ ከጦርነቱ ማግስት ሊታሰብባቸው ይገባል  ያሏቸውን አምስት መሰረታዊ መርሆዎች ይፋ አድርገዋል፤ “አንደኛ ጋዛ የአሸባሪዎች መደበቂያ መሆኗ ማብቃት ይኖርበታል። ሁለተኛ፤  ጋዛ በሃማስ ቁጥጥር ስር መሆኗ ሊያበቃ ይገባዋል ። ሶስተኛ፤ የእስራኤል ሀይል በጋዛ መቆየት አይኖርበትም። አራተኛ፤ የፍስልጤሞች በሀይል መፍናቀል መቆም ይኖርበታል፤ አምስተኛ፤ ጋዛ ከእስራኤል ከበባና ክልከላ ነጻ ሊሆን ይገበዋል” በማለት ለዘላቂ ሰላም በዚህ አቅጣጫ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የአዉሮጳ ህብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦርየልምስል Press Office, Albania Premiership

የህብረቱ የውጭ ግንኑነት ሀላፊ ሚስተር ቦርየልም በመክፈቻ ንግግራቸው፡ የፍልስጤምና እስራኤል  ችግር ይህን ይህል ግዜ መቆየቱና እዚህ ደረጃ መድረሱ የጋራ የፖለቲካና የሞራል ኪስራ ውጤት መሆኑን አውስተዋል፤ ” በአሁኑ ወቅት በመካከኛው ምስራቅ የእስራኤልና የፍልስጤም ህዝቦች እየከፈሉት ያለው ዋጋ የጋራ የፖለቲካና የሞራል ውድቀት ውጤት ነው” በማለት ለችግሩ የሁለት አገሮችንና  መንግስታትን ጎን ለጎን መፈጠር ወይም ( ቱ ስቴት ሶሉሺን”  የሚለው ሀስብ  ቢወሳም ለተግብራዊነቱ ግን  በሙሉ ልብ ጥረት ያልተደረገ መሆኑን በመጥቀስ አደራዳሪና ሸምጋይ የሆኑ አካላትን ስም ሳይጠቅሱ ወቅሰዋል፡፤ አያይዘውም፤ “ ለችግሩ ፖለቲካዊ እንጂ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም በማለት በጦርነት አስከፊ ሰባዊ ቀውስ መፍጠር ይቻላል እንጂ መፍትሄ ማምጣት እንደማይቻል አስታውቀዋል። 

ገበያው ንጉሤ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW