1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፑንትላንድና  የሶማሌላንድ የረሃብ አደጋ

ሐሙስ፣ ግንቦት 3 2009

በጎርጎሮሳዊዉ በ1991 «የሶማሌ ላንድ ሪፐብሊክ» የሚል መንግሥት የመሠረችዉ ሰሜን ሶማሊያ በአፍሪቃ ቀንድ በረሃብ ከተጠቁት ሀገሮች አንዷ ናት።የርዳታ ድርጅቶች እንደሚገምቱት ዓለም አቀፍ ዕዉቅና የተነፈገዉ መንግስት በሚመራት ሶማሊ ላንድ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ፈላጊ ነዉ።

Horn von Afrika Dürre | verendete Ziegen in Somaliland
ምስል Arndt Peltner

Hunger in Puntland and Somalia - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

በአንዳድ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ ድርቁን ያስከተለዉ ችግር በጋራ ለመቋቋም እየተደራጁ ነዉ።አሕመድ ሁሬ ድርዬ ማሕበረሰቡ ከመሠረታቸዉ ማሕበራት አንዱን  ይመራሉ።አህመድ በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ዲላ በተባለች አነስተኛ ከተማ ነዋሪ ናቸዉ።እሳቸዉ እንደሚሉት  በአካባቢያቸዉ ለሰዉም ይሁን ለእንስሳት ንጹህ ዉሃ ፤ምግብና መጠለያ እንዲሁም መድሃኒት ባለመኖሩ የተጎጂዉ ህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻበ መጥቷል።እንሳሳትም ቢሆን እያለቁ ነዉ ።በጊዜ እርዳታ ካልተገኜ ሁኔታዉ አደገኛ በመሆኑ በሰወች ላይም የሞት አደጋ ሊከሰት ይችላል  ሲሉ ስጋታቸዉን ገልጸዋል።
ሌላኛዋ የአካባቢዉ ነዋሪ ሳህራ ሃዋድል ሃጅ  ድርቁ ከመከሰቱ በፊት የበርካታ ፍየሎች ባለቤት ነበረች  በአሁኑ ጊዜ ግን ጥቂት ብቻ ቀርተዋል ትላለች።
« እዚህ የመጣሁት ከ5 ወር በፊት ነዉ።ቀደም ሲል ከልጆቼ ና ከከብቶቼ ጋር በምስራቃዊዉ ክልል ረሃብ ከመከሰቱ በፊት ተሰድጀ ነበር ።500 ከብቶች ነበሩኝ አሁን ግን 30 ብቻ ቀርተዋል።»
ራህል ኩዉድሃሪ የሀገሪቱ መንግስት የእርዳታ ድርጅት ሰራተኛ ናቸዉ  በሀገሪቱ  ባለፉት ሶስት የዝናብ ወቅቶች ያጋጠመዉ የዝናብ እጥረት ህብረተሰቡን ለከፋ የረሃብ አደጋ  ዳርጎታል።እሳቸዉ እንደሚሉት በሶማሊያ ድርቅ የተለመደ ቢሆንም የኮሌራ በሽታና ሌሎች በምግብ  እጥረት ሳቢያ የሚከሰቱ  በሽታወች  ችግሩን ተደራራቢ አድርጎታል። አብዛኛዉ የህብረተሰብ ክፍል የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፈላጊ ነዉ ይላሉ።
«በጥቅምትና በመስከረም 2016 አመተ ምህረት ሶስተኛዉ የዝናብ ወቅት እንደማይኖር ለኛ ግልጽ ነበር ።በሶማሊያ ለብዙወቻችን ረሃብ የተለመደ ነገር ነዉ።ነገርግን በዚህ አመት በተለይም ከጥር ወር ጀምሮ  በነዚህ ሶስት የዝናብ ወራት ዝናብ በመጥፋቱ እያንዳንዱ ሰዉ በረሃብ እንዲጠቃና ለእርዳታ ብቻ ጥገኛ ስንዲሆን አድርጎታል።»
የሀገሪቱ መዲና ሀርጌሳም የረሃብ አደጋ ካጠላባቸዉ ቦታወች አንዱ ነዉ። ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል የከተማዋ ነዋሪወች  ለአደጋዉ ተጋልጠዋል ።በርካታ እናቶች፣ ነብሰ ጡር ሴቶችና ህጻናት  በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተጎዱ በመሆናቸዉ የጤና ማዕከላት በአብዛኛዉ በእነዚህ ታካሚወች የተጨናነቁ ናቸዉ።
ጎርጎሮሳዉያን 1998 ከሶማሊያ ተነጥላ ራሷን እንደሀገር ማስተዳደር የጀመችዉ  ፑንትላንድም በድርቅ አደጋ ክፉኛ ተጠቅታለች።ለወትሮዉ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር የሚታወቁት የአካባቢዉ አርብቶ አደሮችም ከብቶቻቸዉ በማለቃቸዉ እርዳታ ፍለጋ አንድ ቦታ መስፈር ግድ ሆኖባቸዋል።።በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘዉ ደንጎራዬ  ከተማና የስኩሬ መንደር አርብቶ አደሮች ዉሃ፣ መብራትና ህክምና ባይኖርም ወደ 200 የሚጠጉ አባዉራወች  ከነ ቤተሰቦቻቸዉ ዳስ ጥለዉ አንድ ቦታ ተቀምጠዋል።አብዲ ሀሰን የማህበረሰቡ ተጠሪ ናቸዉ ምክንያቱን ያብራራሉ።

«እኛ እዚህ የሰፈርነዉ እርዳታ ለማግኜት ብቻ አይደለም ።ዋናዉ ምክንያታችን የአለማቀፉ ማህበረሰብ እኛን እንደ አንድ ማህበረሰብ እንዲመለከተንም ጭምር ነዉ።ችግራችን በጣም ከፍተኛ ነዉ።»
የፑንትላንድ የአደጋ እርዳታ ድርጅት ሃለፊ አቶ አህመድ አብዱላሂ አብዱራህማን እንደሚሉት በአካባቢዉ 10 ሽህ በላይ የሆኑ ሰወች ለከፋ ረሃብ ተጋልጠዋል።በአሁኑ ጊዜ ድርቁ ያስከተለዉ አደጋ ባለፉት 50 አመታት አጋጥሞ  እንደማያዉቅ ይናገራሉ።
«የእድሜ ባለጸጋወች እንደሚነግሩን ከ1964 አመተ ምህረት ጀምሮ ባለፉት 50 አመታት ዉስጥ እንዲህ አይነት ረሃብ ደርሶ አያዉቅም።የግጦሽ ሳር የለም ዉሃ የለም ። ከብቶቻችን በጣም ከመድከማቸዉ የተነሳ መሸጥ እንኳ አልቻልንም።»
አብዱራህማን ኢነደሚሉት በ2011 ተከስቶ የነበረዉ ድርቅ በተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢወች ብቻ የተከሰተና ከ200 ሺህ በላይ ሰወችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለ ነበር።በአሁኑ ወቅት ግን አሉ አብድራሃማን  የትም ሂዱ የትም ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ የሶማሊያ ህዝብ  የሚላስ የሚቀመስ የለዉም ።

ምስል Arndt Peltner

ፀሐይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW