1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

«የፒፕል ቱ ፒፕል» ዓመታዊ ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥቅምት 16 2016

የፒፕል ቱ ፒፕል ዓለም አቀፍ የጤና ጉባዔና የዕውቅና ሽልማት የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ዕውቀት ሽግግር ለመደገፍ በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመው ፒፕል ቱ ፒፕል 15ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሄደ። ቨርጂኒያ ውስጥ ሰሞኑን በተካሔደው ጉባዔ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎችና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈውበታል።

Symbolbild Literatur Antike Bücher
የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ዕውቀት ሽግግር ለመደገፍ በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመው ፒፕል ቱ ፒፕል 15ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሄደ። ፎቶ፦ የዕውቀት ክምችት መጽሐፍት፤ ከማኅደርምስል፦ VeSilvio

«ፒፕል ቱ ፒፕል»15ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሂዷል

This browser does not support the audio element.

የፒፕል ቱ ፒፕል ዓለም አቀፍ የጤና ጉባዔና የዕውቅና ሽልማት የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ዕውቀት ሽግግር ለመደገፍ በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመው ፒፕል ቱ ፒፕል 15ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሄደ። ቨርጂኒያ ውስጥ ሰሞኑን በተካሔደው ጉባዔ ከኢትዮጵያየተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎችና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈውበታል። ጉባዔው የሴቶች ጤና ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በስራቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች ከድርጅቱ የተበረከተላቸውን ዕውቅና መቀበላቸውን የድርጅቱ መስራችና ፕሬዝደንት ዶክተር እናውጋው መሐሪ ለዶይቼ ቨለ ገልጸዋል።

ፒፕል ቱ ፒፕል የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ የትምህርትና የሙያ ሽግግር በማድረግ ለመደገፍ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከተቋቋመ 25 ዓመት ሆነው። በኢትዮጵያ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንም በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ከፒፕል ቱ ፒፕል እንቅስቃሴዎች መኻከል፣ በየዓመቱ የሚያካሄደውና በጤና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተጠቃሽ ነው።ጉባዔው የሚያበረታታ ስኬት የተመዘገበበት እንደሆነ የሚናገሩት ፕሬዚዳንቱ ዶክተር እናውጋው፣ በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ አገር በቀል መፍትሔዎችን ማፈላለግ እንዲቻል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የፒፕል ቱ ፒፕል ዓለም አቀፍ የጤና ጉባዔና የዕውቅና ሽልማት የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ዕውቀት ሽግግር ለመደገፍ በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመው ፒፕል ቱ ፒፕል 15ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሄደምስል፦ P2P

«ፒፕል ቱ ፒፕል፣ በዓለም አቀፍ ከመቶ ሺ በላይ አባላት አሉት። አንዱ ትልቁ ፒፕ ል ቱ ፒፕል እንደ ድልድይ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያ ዕውቀትና ቴክኖሎጂን የሚገባበ ት መንገድ መስራት ነው። እኛ አሁን ትልቁ የምንሰራው፣ ትራያንጉላር ትብብር፣ ማለት የሀገር ውስጥ ተቋማት፣ ውጭ ያሉት ኢትዮጵያውያን ደግሞ የምዕራቡን ተቋማትም እነዚህ አንድ ላይ ቢሰሩ፣ ሃገር በቀል መፍትሔዎች፣ በሀገሪቱ ላይ እንዲመጣ የሃገሩን ሰርዶ በሃገሩ በሬ የሚባለው ማለት ነው። እና እኛ ከዚህ ሆነን፣ ሃብት ማሰባሰብ ከጓደኞቻችን ጋር አብሮ መስራት በየክልሉ ዛሬ ባህር ዳር አካባቢ ምንድን ነው ያለው? አርሲ አካባቢ ምንድን ነውያለው? እና ይህንን ነገር እንደዚያ ያለ ነገር በትኩረት ተግባራዊ የሆነ ነገር ላይ እናተኩርና ኢትዮጵያ ካሉት ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን።»

ፒፕል ቱ ፒፕል፤ ተሸላሚዎችምስል፦ P2P

ከዚህ በተጨማሪ፦ «ሴቶችን በማብቃት፣ የጤና እንክብካቤን መለወጥ» በሚል መሪ ዐሳብ በተካሄደው በዚሁ ጉባዔ፣ በሰላምና በግጭት ጊዜ ህክምና እና ጤና አጠባበቅ ላይ የተደረጉ ውይይቶች፣ በአስቸጋሪ አካባቢዎች የጤና አጠባበቅ መፍትሔዎችን ለማቅረብ የሚያስፈልገዉን የመቋቋም እና የመላመድ ችሎታ ይፋ መደረጋቸውም ተመልክቷል።

የሦስት ማዕዘን ሽርክና ጽንሰ ሐሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን ጤና በማሳደግ ረገድ ያለው ጠቀሜታ ለመዳሰስ መቻሉም ተገልጿል። በዚሁ ጉባኤ በላቀ ስራቸው ውጤት ያስመዘገቡ ባለሙያዎች፣ ከፒፕል ቱፒፕል የተበረከተላቸውን ዕውቅና ተቀብለዋል። «በየዓመቱ የተለየ ስራ የሰሩትን፣ በተለያየ ዘርፍ የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማት፣ በኮሚኒቲ አገልግሎት ሽልማት፣ በሳይንስ ላይ የተለየ ስራ የሰሩትን በየዓመቱ ዕውቅና እንሰጣለን። እና የዚህ ዓመት የራይዚንግ ስታር ሽልማቱን ዶክተር ጴጥሮስ፣ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ነው ያገኙት።»

ፒፕል ቱ ፒፕል፤ 5ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ አካሄደምስል፦ P2P

 የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ፣ በማደግ ላይ ያለ ኮከብ በሚል ስለተበረከተላቸው ሽልማት ጠይቀናቸው የሚከተለውን መልሰዋል። «እውነቱን ለመናገር ጊዜዬን በከንቱ የማጠፋ ሰው አይደለሁም። የሰው አገርን ነው የተማርኹት ፊንላንድ። ሰዎች አገራቸውን እንዴት እንደቀየሩ ለአገራቸው ዋጋ እንዴት እንደሚከፈሉ ከዚያ ያንን ስፕሪት ይዤ መጥቼ ስለነበር፣ በተቻለ መጠን ጊዜዬን ትክክለኛ ስራዬ ላይ ለማሳለፍ ጥረት የማደርግ ሰው ነበርኹ።ለዚህ ሽልማት ቦርዱ ወስኗል ብለው ሲነግሩኝ ማመን አቃተኝ።» ሌሎች ሽልማት ከተሰጣቸው መኻከል፣ ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የሕይወት ዘመን ስኬት ተሸላሚ ሆነዋል። ፕሮፌሰር ጥላሁን በካሊፎርኒያው ዴቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ህክምናና የቫይሮሎጂ ሳይንስ ኤሜሬትስ ፕሮፌሰር ናቸው ።

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW