1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፓሪሱ ስምምነት ተግባራዊነት

ማክሰኞ፣ መስከረም 17 2009

ባለፈዉ ዓመት ፓሪስ ላይ ከስምምነት የተደረሰዉ ሃገራት የሙቀት አማቂ ጋዞችን የመቀነስ ቁርጠኝነት አሁን በርካታ ሃገራት በየምክር ቤታቸዉ ተቀብለዉ እያጸደቁት መሆኑ ከሰሞኑ የተሰማ አዎንታዊ ዜና ነዉ።

Kohlekraftwerk Mehrum
ምስል picture-alliance/dpa/Julian Stratenschulte

የፓሪሱ ስምምነት ተግባራዊነት

This browser does not support the audio element.

 

 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ እና የቻይናዉ ሺ ዢንፒንግ የቡድን 20 ሃገራት ስብሰባ ከመካሄዱ አስቀድመዉ ነበር፤ የፓሪሱን ስምምነት ማጽደቃቸዉን ያሳወቁት።  የሁለቱ ግንባር ቀደም የዓለማችን ከባቢ አየር በካዮች ርምጃም በዘርፉ በጎ ነገር ለማየት ሲጥሩ ለቆዩት ባለሙያዎች እፎይታን ፈጥሯል። በአሜሪካን ለአካባቢ ተፈጥሮ ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥናት እያደረጉ የሚያቀርቡ ተመራማሪዎች ኅብረት የስልትና የፖሊሲ ዳይሬክተር አልደን ሜየር እንደሚሉትም፤ እስካሁን ባለ ግዙፍ ኤኮኖሚ እና ኢንደስትሪ ሃገራት የፓሪሱን ስምምነት ማጽደቃቸዉ ትልቅ ነገር ነዉ። የፓሪሱ ስምምነት በሥራ እንዲተረጎም ዓለማችንን የሚበክሉ ጋዞችን በብዛት ከሚለቁት ሃገራት ቢያንስ 55ቱ ሊያጸድቁት ይገባል። በተመድ 71ኛ ጉባኤ ላይ ስምምነቱን መቀበላቸዉን በማጽደቅ መግለጻቸዉ የተነገረላቸዉ 31 ሃገራት ናቸዉ። በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢ ተፈጥሮ ላይ የሚያተኩረዉ ዘርፍ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጌታቸዉ አሰፋ ርምጃዉ ትልቅ የዜና ሽፋን ስላገኘበት ምክንያት እንዲህ ያስረዳሉ።

መፈረሙስ ተፈረመ፤ መጽደቁም እንዲሁ። ዋናዉ ግን በተግባር የመዋሉ ጉዳይ ነዉ። 

ምስል Reuters/H. Hwee Young

ምንም እንኳን ዩናይትድ ስቴትስ ይህን ስምምነት ማጽደቋን ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ኦባማ ቢገልጹም፤ ተግባራዊነቱ ዶክተር ጌታቸዉ እንዳሉት የቀጣዩ ፕሬዝደንት ማንነት እና አቋም ይወስነዋል። ያመጣላቸዉን ባደባባይ በመናገር በብዙዎች ዘንድ በጥያቄ የሚታዩት ፕሬዝደንታዊዉ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እንደተመኙት በፉክክሩ አሸንፈዉ ስልጣን ቢይዙ ሊሆን የሚችለዉን በአሜሪካን ለአካባቢ ተፈጥሮ ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥናት እያደረጉ የሚያቀርቡ ተመራማሪዎች ኅብረት የስልትና የፖሊሲ ዳይሬክተር አልደን ሜየር ተንትነዉታል። የታሰበዉን ዉጤት ለማስገኘት ይህ ምን ማለት ይሆን? በአሁኑ ጊዜ ለሚታየዉ የዓለም ሙቀት መጨመርስ የሚኖረዉስ  ፋይዳ? ከድምጽ ዘገባዉ ዝርዝሩን ያድምጡ!

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW