የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 ፤ ኢትዮጵያ በ 800 ሜትር ሜዳልያ አገኘች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2016ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በሴቶች የ 800 ሜትር ርቀት ለመጀመርያ ጊዜ የሜዳልያ ባለቤት ሆነች። ትናንት ምሽት በፓሪሱ ስቴድዮም በተካጌደዉየ 2024 የኦሎምፒክ ዉድድር፤ የሴቶች የ 800 ሜትር የሩጫ ዉድድር ፍፃሜ ኢትዮጵያዊትዋ አትሌት ጽጌ ድጉማ አንድ 1 ደቂቃ 15 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ዉጤት የግልዋን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ፤ አጠናቃለች። አትሌት ጽጌ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያን ለማስመዝገብ ችላለች። ይህም በርቀቱ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ዉድድር ላይ አዲስ ታሪክ ለመሆኑ ችሏል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያዉያን ሴት አትሌቶች፤ ሜዳልያ ሊስመዘግቡበት እንደሚችል ተጠብቆ የነበረዉ፤ የ5000 ርቀት ፍጻሜ ዉድድር፤ ዉጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌቶች፤ እጅጋየሁ ታየ 6 ኛ ፤ መዲና ኢሳ 7 ኛ ፤ ጉዳፍ ፀጋዬ 9 ኛ ሆነዉ ዉድድሩን አጠናቀዋል። ኢትዮጵያዉያኑ ሴት አትሌቶች በዉድድሩ ላይ የአቅም ዉስንነት የታየባቸዉ እና፤ የተከተሉትም የአሯሯጥ ስልት ፤ ለተመዘገበዉ ዉጤት ምክንያት ፤ እንደሆነም ተነግሯል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ