1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕላስቲክ ዳግም ማምረቻ ፋብሪካ

ማክሰኞ፣ መስከረም 10 2015

አራት መቶ ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የተመሰረተው ይህ ፋብሪካ በቀጣይ በግብዓትነት የሚጠቀምበትን ያገለገሉ ፕላስቲክ የውሀ መያዣ ኮዳዎችን ከድሬደዋ በተጫማሪ ከምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች አካባቢዎች ለማሰባሰብ እቅድ መያዙን አስታውቋል።

Ätiopien Kunststoff-Recycling-Fabrik in Dire Dawa
ምስል Mesay Teklu/DW

«ፋብሪካዉ ለ10 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል» ስራ አስኪያጅ

This browser does not support the audio element.

             
አገልግሎት የሰጡ የፕላስቲክ የውሀ ኮዳዎችን ፈጭቶ ዳግም  አገልግሎት እንዲሰጡ ወይም Recycle የሚያደርግ ፋብሪካ ድሬደዋ ዉስጥ ተከፈተ። ኤም አይ ጂ ተብሎ የሚጠራዉ ፋብሪካ ኃላፊዎች እንዳሉት ፋብሪካቸዉ በቀን 24 ቶን ፕላስቲክ መፍጨት ይችላል።የሚጣሉ የፕላስቲክ የውሀ ኮዳዎች ለማስወገድና በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ብክለት ለመከላከል ይረዳልም።

በድሬደዋ ወደ ስራ የገባው ኤምአይጂ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አበበ መንገሻ ፋብሪካው በቀን ሃያ አራት ቶን ፕላስቲክ የመፍጨት አቅም እንዳለው ጠቅሰው በጥሬ አቅርቦት እና ምርቱ ለገበያ በሚቀርብበት ሁኔታ ካይ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አራት መቶ ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጭ ወደ ስራ መግባቱ የተነውገረው የዚህ ፋብሪካ ፕሮጀክት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳለው ኢንጅነር አበበ ጠቁመዋል።የድሬደዋ አስተዳደር የስራ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለከተማዋ ውበት እና ፅዳት እና ውበት መጠበቅም ሆነ በስራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ አስረድተዋል።በከተማዋ ተወላጅ ወጣቶች ወደ ስራ የገባውን ፕሮጀክት ስራ ያስጀመሩት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ስራው እንዲሳካ በመንግስት የተደረገውን ድጋፍ ጠቅሰው በቀጣይም ይኸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አራት መቶ ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የተመሰረተው ይህ ፋብሪካ በቀጣይ በግብዓትነት የሚጠቀምበትን ያገለገሉ ፕላስቲክ የውሀ መያዣ ኮዳዎችን ከድሬደዋ በተጫማሪ ከምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች አካባቢዎች ለማሰባሰብ እቅድ መያዙን አስታውቋል

መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW