1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትራምፕ አስተዳደር የፕሪቶርያዉ ስምምነትና የአፍሪቃ ቀን ፖለቲካ ዕጣ ፈንታ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ጥር 12 2017

የትግራይ ፖለቲከኞች የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በሙሉእነት እንዲተገበር ምዕራባውያንን በተለይም በአሜሪካ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ይሰማል። የፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የውሉ ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉ የብዙዎች መወያያ አጀንዳ ነው።

የፕሪቶርያዉ የሰላም ስምምነት
የፕሪቶርያዉ ስምምነት ምስል PHILL MAGAKOE/AFP

በትራምፕ አስተዳደር የፕሪቶርያዉ ስምምነትና የአፍሪቃ ቀን ፖለቲካ እጣ ፈንታ

This browser does not support the audio element.

የፕሪቶርያዉ ስምምነት እጣ ፈንታ በትራምፕ አስተዳደር

የትግራይ ፖለቲከኞች እስካሁን በሙሉእነት አልተፈፀመም የሚሉት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በሙሉእነት እንዲተገበር በአጠቃላይ ምዕራባውያንን በተለይም በአሜሪካ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጥሩ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ይሰማል። የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የውሉ ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉ ነጥብ የበርካቶች መወያያ አጀንዳ ነው። በዚህ ጉዳይ ዙርያ የፖለቲካ ተንታኝ አነጋግረናል።

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የፕሪቶርያውየሰላም ስምምነት በርካታ ነጥቦች እስካሁን  አልተተገበሩም የሚሉ በትግራይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ውሉ በሙሉእነት እንዲፈፀም ጫና እንዲፈጥር ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ በተደጋጋሚ ጥሪ ያቀርባሉ። ትላንት የተከበረው የጥምቀት በዓል አስመልክተው መልእክታቸው ያስተላለፉት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ፥ የትግራይ ግዛቶች የተቆጣጠሩ ሐይሎች እንዲወጡና የተፈናቀለው ህዝብ ለመመለስ አስተዳደራቸው እንደሚሰራ ያስታወቁ ሲሆን ይህ ለማድረግ ደግሞ ከአሜሪካ መንግስት ጨምሮ ከአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች በጋራ እንደሚሰራም ገልፀዋል። በትግራይ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እንዲሁ ለፕሪቶርያው ውል ሙሉ ተፈፃሚነት የአሜሪካ መንግስት ጨምሮ ሌሎች አካላት በውሉ ፈራሚዎቾ ላይ ጫና እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ጥሪ ያሰማሉ። የፕሪቶርያው ውል በርካታ እና ወሳኝ ነጥቦች አሁንም ባልተፈፀሙበት መጥቷል የሚሉት አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር በኢትዮጵያ እንዲሁም በአጠቃላይ አፍሪካ ቀንድ ይኖረዋል ተብሎ ስለሚጠበቅ የትኩረት አቅጣጫ የበርካቶች መወያየት አጀንዳ ሆንዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል Matt Rourke/AP/picture alliance

ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኘ አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ቀጣይ የሚጠበቁ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙርያ ፖለቲከኛው እና የሕግ ምሁሩ አቶ ተስፋዓለም በርሃን አነጋግረናል።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW