1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሕገ - መንግሥት ጥሰት አቤቱታ ቀረበበት

ሰኞ፣ ጥር 6 2016

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣው ደንብ ቁጥር 4/2016 የኢፌዴሪን ሕገ - መንግሥት አራት አንቀጾችን የሚቃረን ነው በሚል የሕገ- መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉዳዩ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የዳኝነት አቤቱታ ቀረበ። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ደንብ ለምን አወጣው ?

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምስል Million Haileselassie/DW

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ደንብ ለምን አወጣው ?

This browser does not support the audio element.

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣው ደንብ ቁጥር 4/2016 የኢፌዴሪን ሕገ - መንግሥት አራት አንቀጾችን የሚቃረን ነው በሚል የሕገ- መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉዳዩ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የዳኝነት አቤቱታ ቀረበ። 

አቤቱታ አቅራቢው መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች - ኢትዮጵያ የተባለው ሀገር በቀል የሲቪክ ድርጅት ሲሆን የአቤቱታው መነሻ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያወጣው ደንብ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት  "ኢ- ሕገ መንግሥታዊ ተብሎ የፈረሰው [የክልሉ] ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጎች ተፈፃሚነታቸው እንዲቀጥል ያደረገ በመሆኑ" ነው ይላል። 

አቤቱታው "በኢትዮጵያ እና በክልሉ ሕጎች መሠረት የተቀጠሩ፣ የሰለጠኑ፣ እና ለዓመታት ያገለገሉ የፖሊስ አባላት በትጥቅ ትግል አልተሳተፉም በሚል ከሥራ ማባረሩን ወይም ወደ ሥራ እንዳይመለሱ" እና ጡረታ መከልከላቸውን ይጠቅሳል። 

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር የተመሠረተው በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት በተፈራረሙት ግጭት የምቆም ሥምምነት መሠረት ነውምስል Million Haileselassie/DW

ይሁንና ይህ ሕግ የወጣው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ሕገ - መንግሥታዊ አይደለምበሚል በፈረሰው የክልሉ ምክር ቤት በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም ሲል የሲቪክ ድርጅቱ ጉዳዩን ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባኤ አቅርቦታል።//

ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የቀረበው አቤቱታ ጭብጥ

ቅድሚያ ለስብዓዊ መብቶች - ኢትዮጵያ የተባለው የሲቪክ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መብርሂ ብርሃነ ተቋማቸው ለሕገ - መንግሥት አጣሪ ጉባሬ ያስገባው አቤቱታ መነሻ ምክንያት የትግራይ ክልል ጉዜያዊ አስተዳደር "መሠረታዊ" ያሉትን የሕገ - መንግሥት ጥሰት በመፈፀሙ ነው። 

"መሠረታዊ የሆኑ የሕገ - መንግሥት የበላይነትን የሚጥሱ አንቀጾችን ይዞ ነው የወጣው ደንቡ። በዋናነት ሦስት ነገሮች ናቸው። አንደኛ የዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብትን ትላልፎ በተለይ ከጥቅምት 24/ 2013 እስከ ሕዳር 30 /2015 ባሉት ጊዜያት ውስጥ የመንግሥትም ይሁን የግል ሠራተኛ ምንም አይነት ክስ እንዳያቀርቡ [ ያልተከፈለ ደሞዝን በሚመለከት] ክስ ቀርቦ ከነበረም ተቋርጦ ባለበት እንዲሆን የሚል" ነው። 

የሲቪክ ድርጅቱ በጦርነቱ ወቅት ሕገ - መንግሥታዊ አይደለም በሚል ሕጋዊነቱን አጥቷል ባለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በወጣ ዐዋጅ መሰረት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ ከ 1 ሺህ በላይ የትግራይ ክልል ፖሊስ አባላት የነበሩ ሰዎች ከሥራ ተባረው በችግር ላይ መሆናቸው ሌላኛው የአቤቱታው መነሻ ነው ብሏል።
በክልሉ ወጥተው በነበሩ የአስቸካይ ጊዜ ሕጎች ፍርደኛ ሆነው በእሥር ላይ የሚገኙ ሰዎች ወደ ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ በመሄድ የይግባኝ መብታቸውን እንዳይጠቀሙ የሚከለክል መሆኑ ሌላኛው ተጨማሪ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያወጣው ደንብ የኢፌዴሪ ሕገ - መንግሥት አንቀጽ 9 ፣ አንቀጽ 37 ፣ አንቀጽ  80 እና አንቀጽ 55ን መጣሱንም ተናግረዋል። 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት በከፊልምስል Million Hailesilassie/DW

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ደንብ ለምን አወጣው ? 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ደንብ ሊያወጣ የቻለበት ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚችል አቶ መብርሂ ግምታቸውን ገልፀዋል።
"ከመንግሥት ሠራተኞች እና ከግል ሠራትኛች ጋር ተያይዞ የደሞዝ ጥያቄ በየጊዜው እየተጠየቁ ሲመጡ ይህንን በሕግ አውጥተን ለምን አንገድበውም የሚል አቋም የወሰዱ ይመስልኛል" 

ሕዳር 28 ቀን 2016  ዓ. ም በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተፈረመው እና "ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሕጎች ወደ መደበኛ ሕግ ለመምለስ የወጣ የመሸጋገሪያ ደንብ" በሚል የወጣው ሕግ "ወደ መደበኛ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መጠናከርን ሊያግዝ የሚችል እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት" ይህ ደንብ መውጣቱን ይገልፃል።

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW