1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
መገናኛ ብዙኃንኢትዮጵያ

የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ ያሽቆለቆለበት ምክንያቱ ምን ይሆን?

እሑድ፣ ግንቦት 3 2017

ኢትዮጵያ የፕሬስ ምዘና ከተደረገባቸው 180 አገራት መካከል ቁልቁል 145ኛ ላይ መገኘቷ ከሰሞኑ ተዘግቧል ። በኢትዮጵያ የዛሬ ሰባት ዓመት ግድም ብሩኅ ተስፋ አንጸባርቆ የነበረው የፕሬስ ነጻነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እያሽቆለቆለ መሆኑ ይነገርለታል ። ሳምንታዊውን ሙሉ የውይይት ዝግጅትን በድምፅ ማድመጥ ይቻላል ።

ኢትዮጵያ በጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት  ዘገባ የፕሬስ  ምዘና ከተደረገባቸው 180 አገራት መካከል ቁልቁል 145ኛ ላይ ትገኛለች
ኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ዘገባ የፕሬስ ምዘና ከተደረገባቸው 180 አገራት መካከል ቁልቁል 145ኛ ላይ ትገኛለች ።ምስል፦ IMAGO/imagebroker

የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ ማሽቆልቆሉን ቀጥሏል

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ  የዛሬ ሰባት ዓመት ግድም ብሩኅ ተስፋ አንጸባርቆ የነበረው የፕሬስ ነጻነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እያሽቆለቆለ መሆኑ ይነገርለታል ። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ይፋ በሚያደርጓቸው የፕሬስ ነፃነት መለኪያዎች በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ከድጡ ወደ ማጡ እየተንሸራተተ መሆኑን አሳስበዋል

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (Reporters Without Borders) ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ዘገባ፦  ኢትዮጵያ  የፕሬስ  ምዘና ከተደረገባቸው 180 አገራት መካከል ቁልቁል 145ኛ ላይ ትገኛለች ።

ከጎርጎሪዮሱ ያለፈው 2024 ዓመት መዘርዝር ከ141ኛ ደረጃ በአራት ዝቅ ብላለች ማለት ነው እንደ ዘገባው ። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ አምስት ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ እንደሚገኙ በዘገባው ጠቅሷል ። በርካታ ጋዜጠኞች እስር እና እንግልትን በመፍራት ከአገር መሰደዳቸው ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ተዘግቧል ።

አገር ቤት ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች የተለያዩ ጫናዎች እና እንግልቶች እንደሚደርስባቸው በመጥቀስ እያማረሩ ነው ። የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ቢሯቸው እንደሚመዘበር፤ ኮምፒውተር፣ ካሜራ እና ስልክን የመሳሰሉ መሣሪያዎቻቸው እንደሚወሰዱም እየተናገሩ ነው ። ለመሆኑ፦ «የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጵያ ያሽቆለቆለበት ምክንያቱ ምን ይሆን፦ የዛሬው እንወያይ መሰናዶዋችን ዐቢይ ትኩረት ነው ። 

ሙሉውን ውይይት በድምፅ ማጫወቻው ማድመጥ ይቻላል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW