የፕሬዚደንት ቮልዶሚር ዘሌንስኪ ድንገተኛ የኔቶ ጉብኝት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚየር ዘለንስክይ ትናንት ሳይታሰብ በብራስልስ የስሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ የመከላከያ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተገንተው፤ ለዩክሬን የሚደረገው ሁለንተናዊ እርዳታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተማጸኑ መሆኑ ተገልጿል። ሁለት ዓመት ሊሞላው ወራት የቀሩት የዩኪሬን ጦርነት በዋናነት በአሜሪካ መራሹ የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት የሚደገፍና የአውሮፓ ትኩረትም ያልተለየው ቢሆንም፤ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪን ትናንት በድንገት በብራስሉ የኔቶ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያስገኛቸው ግን ባለፈው ቅዳሜ የተጀመረው የሀማስ ኢስራኤል ጦርነት፤ ለዩክሬን የሚሰጠውን ድግፍ እንዳይቀንሰው በመስጋት ሳይሆን እንድላቀረ ተገምቷል።የኔቶ አባል ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ፍጻሜ የዩክሬን፤ሩሲይ ጦርነት መቋጫው እየራቀ ሲሄድ የመንግስታቱ ድጋፍ እየቀነሰ ሊሄድ እንደሚችል በቅርቡ በአሜርካ ምክርቤት የተያውና በአውሮፓም በስሎቫኪያ በተደረገ ምርጫ ለዩኪሬን የሚስጥን የመሳሪያ እርዳታ የሚቃወም ፓርቲ ማሸንፉ ማሳያ ሁነው እየተጠቀሱ ባለበት ወቅት፤ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረው ሁኒታ ፕሬዝድንት ዝለንስኪን ማስጋቱ ተጠባቂ ነው፤ እንደታዛቢዎች አስተያየት።
ዘለንስኪ ግን ቀድመው ዋናዋ አሸባሪና የአሸባሪዎች ደጋፊ ጦርነት የከፈተችባቸው ሩሲያ በመሆኗ ሁለቱንም አሸባሪዎች በአንድነት መዋጋት እንደሚገባ በማሳሰብ፤ ምራባውያን በምንም አይነት አይናቸውን ከሩሲያ ላይ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያም ማሳሰቢያም ሲሰጡ ነው የተሰሙት። “ ሃማስም ሩሲያም አንድ አይነት አሸባሪዎች ናቸው ። ልዩነቱ ኢስሬኤልን ያጠቃው አሸባሪ ድርጅት ነው ዩኪረንን ያጠቃው ግን አሸባሪ መንግስት ነው። ከዚህ ውጭ በአላማም በድርጊትም አንድ ዓይነት ናቸው በማለት ሁለቱንም በአንድነት መታገልና መዋጋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን ዘላቂ ድጋፉ ይቀጥላል አለ
በትናንትናው እለትም ዘለንስኪ በብራስልስ ተገንተው የዩክሬን ጉዳይ በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ እንዳልሆነና በተለይ በአሁኑ ክረምቱ እየገባ ባለበት ወቅት አሳስቢና የሁልውና ጉዳይም መሆኑን በመግለጽ ባስቸኳይ አስፈላጊዎቹ መሳሪያዎች እንዲደርሷቸው ጠይቀዋል። “ በክረምቱ ግዜ ከፍተኛ ተግዳሮት ነው የሚገጥመን፤ በእርግጥ ዝግጁ ነን፤ ግን የናንተ ድጋፍ ከመቸውም ግዜ ይበልጥ ያስፈልገናልና፤ ይህን ለመጠይቅ ነው እዚህ የተገኘሁት በማለት፤ ጥያቄው የህልውና ጭምር መሆኑን አስገንዘበዋል። የኔቶ ዋና ጸሀፊ ሚስትር ያን ስቶልቴንበርግ በበኩላቸው፤ “ የናንተ ጦርነት የኛ ጦርነት ነው። የንንተ ደህንነት የኛ ደህንነት ነው፤ የናንተ እሴቶችም የኛ እሴቶች ናቸው” በማለት እስራኤልንም እነሱንም የመርዳት አቅምም ችሎታም ያላቸው መሆኑን አረግግጠውላቸዋል። የኔቶ መከላከያ ሚኒስቶርችም በጋራ መግለጫቸው ለዩክሬን የሚስጠው እርድታ እንደማይቀንስና ተጠክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከቤልጀየም ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተርና አሌክሳንደር ደክሮን ጋርም ተገናኝተው ቤልጅየም ስለምትስጠወ እርድታ ተወይይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ደክሮን፤ ቤልጅየም ኤፍ 16 ተዋጊ አውሮፕላን ለዩክሬን እንደምትሰጥም ቃል የገቡ ሲሆን፤ ይህ ግን በሚቀጥለው ምርጫ የሚቋቋመው መንግስት ሲያጸድቀውና እ እ እከ2025 በኃላ እንደሚሆን ነው የተገለጸው። ከዚሁ ጋር ሚስተር ደክሮን፤ ከሩሲያ ንብረት በታክስ የሚሰበሰብ ገንዘብ ለዩኪረን ገቢ እደሚደረግ ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አረጋግጠውላቸዋል።የአዉሮጳ ሕብረት ሚንስትሮች ለዩክሬን ተጨማሪ ድጋፍ ሰጡ
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከጠቅላይ ሚስተር ደክሮን ጋር በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከአጋሮቻቸው የሚደርሳቸው ድጋፍ እንዳይቀንስ ስጋት ያለብቸው መሆኑን አልሸሸጉም፡ “ እውነቱን ለመናገር ጥያቄየ የምታደርጉል ድጋፍ አሁን ካለው ይቀንስ ይሆን? የሚለው ነው። በእርግጥ የሚሉት አይሆንም ነው። ግን ማን ያውቃል ፤ ማንም አያውቅም።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ