1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዓመታዊ የመጀመሪያ ንግግር

ረቡዕ፣ የካቲት 23 2014

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ ፕሬዚደንቶች ካለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት አንስቶ በየዓመቱ ኮንግሬስ ፊት ቀርበው የሚያደርጉትን ንግግር ትናንት አሰምተዋል። ፕሬዚደንቱ በዚሁ የመጀመሪያ ንግግራቸው ስለሀገራቸው እና ስለዓለም ወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ በመስጠት ማብራሪያም አሰምተዋል።

USA Präsident Joe Biden Rede zur Lage der Nation
ምስል Jabin Botsford/Getty Images

የንግግራቸው ዐቢይ ትኩረት የዩክሬን ሩስያ ጦርነት ነበር

This browser does not support the audio element.

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሀገሪቱ ፕሬዚደንቶች ካለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት አንስቶ በየዓመቱ ኮንግሬስ ፊት ቀርበው የሚያደርጉትን ንግግር ትናንት አሰምተዋል። ፕሬዚደንቱ በዚሁ የመጀመሪያ ንግግራቸው ስለሀገራቸው እና ስለዓለም ወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ በመስጠት ማብራሪያም አሰምተዋል። የፕሬዚደንቱ ዓመታዊ ንግግር ላይ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት፤ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ርምጃ እና የአውሮጳ ብሎም የኔቶ አቋምን የዳሰሰም ነበር። የፕሬዚደንቱ የመጀመሪያ ዓመታዊ ንግግርን የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ተከታትሎታል። ፕሬዚደንቱ በትናንቱ ንግግራቸው፦ የሀገር ውስጥ የኤኮኖሚ ጉዳይ፤ የኮቪድ ወረርሽኝ ሥርጭት፤ የዋጋ ግሽበት እና ሥራ አጥነትን እንዲሁም የሕገወጥ ጦር መሣሪያዎችን መቆጣጠርን የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ አተኩረዋል። በዋናነት እና ባልተለመደ መልኩ ከንግግራቸው አንድ ሦስተና ያተኮሩት በikeሬን እና ሩስያ ጦርነት ጉዳይ ላይ የአሜሪካን አቋም በማንጸባረቅ ነበር። 

ጆ ባይደን በንግግራቸው ወቅት የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲንን ዩክሬን ውስጥ የጀመሩትን ጦርነት በብርቱ ነቅፈዋል። የሩስያ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር ንክኪ ያላቸው ባለሐብቶችን ንብረት ስለማገድም ተናግረዋል። ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ የፈጸመችው ወረራ አስቀድሞ የታሰበበት ነው፤ አውሮጳ እና አሜሪካ በአንድነት ይህን ማሸነፍ መቻል አለበት ብለዋል። በዋናነትም የሩስያ ኤኮኖሚ ላይ ብርቱ ማዕቀብ በመጣል ነው መታገል የፈለጉት።

ሪፐብሊካኑ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአውሮጳ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ እንጥላለን ማለታቸውን ትርጉም አልባ ሲሉ ነቅፈውታል። ቭላድሚር ፑቲንን ብልህ ሲሉ በማወደስ የሀገራቸው መሪዎችን ደካማ በማለት አጣጥለዋል። አሜሪካ ሩስያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማሰቧ በዶናልድ ትራምፕ እና የእሳቸው ደጋፊ ሪፐብሊካኖች ተጣጥሏል። በዚህም አለ በዚያ ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮቿን ዩክሬን ውስጥ እንደማታሰልፍ ዐስታውቃለች።  ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማትሻም ገልጣለች። 

አበበ ፈለቀ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW