1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የፕሬዚዳንት ባይደን የአንጎላ ጉብኝት

ሐሙስ፣ ኅዳር 26 2017

በአንጎላ ለሦስት ቀናት ያድርጉትን ጉብኝት ያጠናቀቁት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን፣በሚቀጥለው ምዕተ ዓመት ለመልማት የሚፈልግ ማንኛውም አገር ሁሉ አፍሪቃ ውስጥ በአጋርነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

Angola Luanda 2024 | Besuch Präsident Joe Biden
ምስል፦ Ben Curtis/AP/dpa/picture alliance

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ባሰሙት ንግግር «ሰላማዊ የኃይል ሽግግር» ይኖራል ብለዋል

This browser does not support the audio element.

የፕሬዚዳንት ባይደን የአንጎላ ጉብኝት

የዓለም መጻዒ ዕድል ያለው አፍሪቃ ውስጥ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ተናገሩ።

በአንጎላ ለሦስት ቀናት ያድርጉትን ጉብኝት  ያጠናቀቁት  የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን፣በሚቀጥለው ምዕተ ዓመት  ለመልማት የሚፈልግ ማንኛውም አገር ሁሉ አፍሪቃ ውስጥ በአጋርነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት

በስልጣን ዘመናቸው የመጨረሻዎቹ ሳምንታት ላይ የሚገኙት ጆሴፍ ባይደን አንጎላን በመጎብኘት  የመጀመሪያው የአሜሪካ መሪ ናቸው።

ፕሬዚዳንት ባይደን ከሦስት ቀናት በፊት የአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ሲደርሱ በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በጋራ ውይይት አድርገዋል።

ባይደን በአንጎላ የነበራቸው ቆይታ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪቃ ጋር ባላት አጋርነት፣በተለይም ደግሞ አሜሪካ ለአፍሪቃ መስረተ  ልማቶች በምታደርገው አስተዋኦ ላይ የተኮረ ነበር።

አንጎላ:- የባይደን የመጨረሻ የአፍሪቃ ጉብኝት

 

የሎቢቶ ኮሪደር

በመሆኑም፤ ፕሬዝደንቱ የሎቢቶ ኮሪደር በመባሌ የሚታወቀውንና ከኮንጎና ዛምቢያ ተነስቶ፣ሎቢቶ ከተሰኘችው የአንጎላ ወደብ የሚደርሰውን የአንድ ሺህ 300 ኩሎ ሜትር የባቡር መንገድ ላይ ጉብኝት አድርገዋል።ይኸው የሎቢቶ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት፣ተሰናባቹ የባይደን አስተዳደር፣በአፍሪቃ የሚያደርገው የመሠረተ  ልማት ጥረት ማዕከል ሆኖ ቆይቷል። 

ለሎቢቶ ኮሪደር አዲስ የስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ትናንት የፋ በተደረገበት ወቅት፣ባይደን በደ ሎቢቶ  በማቅናት ከአንጎላ፣ ዛምቢያና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ መሪዎች ጋር የጋራ ስብሰባ አድርገዋል፤ከመሪዎቹ ጋር በመዘዋወርም ወደቡንም ጎብኝተዋል።

የአፍሪቃ መጪው ብሩህ ጊዜባይደን፣በአንጎላ ቆይታቸው ወቅት ከተመለከቷቸው ታሪካዊ ስፍራዎች መኻከል፣የአንጎላን ብሔራዊ የባሪያ ፍንገላ ዘመን መታሰቢያ ቤተ መዘክር ይገኝበታል።

በዚህ ሙዚየም ባደረጉት ንግግራቸውም፣በባርነት ዘመን የተፈጸሙ ግፎችንች አስመልክተው ሲናገሩ፣ የአሜሪካ የመጀመሪያ ኃጢያቶች ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፣ ጊዜ በአንጎላና በአፍሪቀ በኩል ብሩህ እንደሆነ አመልክተዋል።

የአፍሪቃ መጪው ብሩህ ጊዜባይደን፣በአንጎላ ቆይታቸው ወቅት ከተመለከቷቸው ታሪካዊ ስፍራዎች መኻከል፣የአንጎላን ብሔራዊ የባሪያ ፍንገላ ዘመን መታሰቢያ ቤተ መዘክር ይገኝበታል።ምስል፦ Ben Curtis/AP/dpa/picture alliance

 

ፕሬዝዳንት ባይደንና ተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነጩ ቤተ-መንግሥት ዉስጥ ተገናኙ

"ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ የአፍሪቃ ከንቲባዎች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኜ ብቆይም፣ወደአንጎላ መጥቼ አላውቅም፤ምክንያቱም ወደፊት ምን እንደሚሆን አላውቅም ነበር። መጪው ዕድል በአንጎላ በአፍፍሪቃ ወስጥ እንዳለ አውቃለሁ።"

የባይደን የአፍሪቃ ጉዞ፣ቻይና በአህጉሪቱ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ለመገዳደር ያለመ እንደሆነ የሚናገሩ ተንታኞች አሉ።

ይሁንና፤አንድ ከፍተኛ የስተዳድራቸው ባለሥልጣን ከባይደን የሉዋንዳ ጉዞ በፊት ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ቻይናን ለመተከት እየሞከረች ሳይሆን፣ይልቁንም ከሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ራሷን በተሻለ አማራጭ ለማቅረብ እየሞከረች እንደሆነ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የጀርመን ጉብኝት

የዋይት ኃውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ፤ጆኒ ኪርቢ ሉዋንዳ ውስጥ ለዜና ሰዎች በሰጡት አስተያየት፣ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪቃ ተጨባጭ እና ግልጽ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን መስጠት እንደምትፈልግ ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን፣በአነሰጎላ ቆይታቸው አጽንኦት ሰጥተው እነደተናገሩትም፣በመጪው ጊዜ ከአፍሪቃ ጋር በትብብር መስራት እንደሚጠበቅበት ነው።

"በመጪው ምዕተ ዓመት፣ማደግ የሚፈልግ ማንኛውም ሃገር፣ከሠራተኞች፣ከስራ ፈጣሪዎችና ከንግድ ሰዎች ጋር በመሆን፣እዚህ አፈሪቃ ውስጥ መስራት አለበት። በማህ

ኀበረሰባችን፣ በዩኒቨርስቲዎቻችንና በስፖርቶቻችን፣በሲቪል ማኀበረሰቦቻችንና በህዝቦቻችን መኻከል ያለው ግንኙነት የበለጠ ጥልቀት እንደሚኖረው አምናለሁ፤ለዚህም ትኩረት አድርገን መስራት አለብን።"

በአሜሪካ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ጆ ባይደን በይፋም ባይሆን ፓርቲያቸውን ተሰናበቱ

ፕሬዝዳንት ባይደን፣ እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር ከ2022 እስከ 2025 በመላው አፍሪቃ 55 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ድጋፍ ለማድረግ ቃል መገባቱን አውስተው፣ እስካሁን አስተዳደራቸው ወደ 40 ሚሊዮን መስጠቱን አስታውቀዋል።በአሜሪካ የዲሞክራቲክም ሆነ  የሪፐብሊካሉ ፓርቲ አፍሪቃን አስመልክቶች የጎላ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ልዩነት የሌላቸው በመሆኑ፣መጪው የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የተጀማመሩ ስራዎችን እንደሚያስቀጥላቸው ይጠበቃል።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW