1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወቀሳ

ረቡዕ፣ መስከረም 8 2017

የፖለቲካ አመለካከትን መሠረት ያደረገ ጫና እየደረሰበት እንደሚገኝ የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት ሰኔ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በክልል ምርጫ ከተካሄደ ወዲህ በፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደደሰበት እንደሚገኝ ዐሳወቀ፡፡

Äthiopien Assosa City | Benishangul Gumuz Region
ምስል Negassa Dessalegn/DW

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲ እንግልት

This browser does not support the audio element.

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት ሰኔ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በክልል ምርጫ ከተካሄደ ወዲህ በፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደደሰበት እንደሚገኝ ዐሳወቀ፡፡ፓርቲው በሰኔ 16 ምርጫ በተወዳደረበት መተከል ዞን 3 ለክልል ምክርቤት እና አንድ የህዝብ ተወካዩች ምክርት ቤት ወንበር ማግኘቱን የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ አስታውሰዋል፡፡ ቡሌን በተባለው ወረዳ ተቃዋሚ ፓርቲ መርጣቹሀል ተብሎ የፓርቲው ደጋፊዎች፣ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች ላይ ዛቻ እና ማስራርያ እየደረሰ እንደሚገኝ ገልጸው አባላቱ ለእስር እየዳረጉ እንደሚገኙ አክለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋርናቸው የቡሌን ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት አዛዥ በወረዳው በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ ግለሰብም ሆነ ቡድን በወረዳው የለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በተካሄደው ቀሪና ድጋሚ 6ኛ ጠቅላላ ምርጫ ላይ መሳተፉንና የክልልና የህዝብ ተወካዮች ወንበር ማግኘቱን ያሳወቀው የቦሮ ዴሞክራሲ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት የተቀናጀ ያለው ወከባና ዛቻ በአባላቱ ላይ መድረሱን አመልክተዋል፡፡ ፓርቲው ምርጫ ባሸነፈበት የመተከል ዞን ቡሌን ወረዳ የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ወቅቶች እንደሚታሰሩና ከልዩ ልዩ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተሳትፎ መከልላቸውን የፓርቲው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ተሰማ ለዶቸቨለ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው እንዳሳወቁት በወረዳው በንግድ፣በግብርና እንዲሁም በመንግስት ስራ ላይ የተሰማሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ላይተፎካካሪ ፓርቲ ደግፋቹሀል፣መርጣቹሀል በሚል ማስፈራሪያና ዛቻ እንደረሰባቸው ነው ፡፡ የፓርቲውን አባላት መብት በመንፈግ የፖለቲካ አመለካትን መሰረት ያደረገ ጫናዎች እየደረሱበት እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ በፓርቲው ላይ የደረሱ የመብት ጥሰቶችን የሰብአዊ መብት ተቋማት እንዲከታተሉም ሀሳብ ማቅረባቸውን አቶ ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Negassa Dessalegn/DW

በመተከል ዞን ቡሌን ወረዳ በፓርቲው አባሎች ላይ ደርሷል የተባለውን እስራት እንዲሁም ሌሎች ፓርቲው ያነሳቸውን ቅሬታዎችን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው የወረዳው ፖሊስ በቡሌን ወረዳ በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ ሆነ በደል የደረሰበት ግሰለብም ሆነ ቡድን የለም ሲል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ብርሀኑ ኤጄታ በአካባቢው የፖለቲካ ድርጅቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ መሳተፋቸውን በመግለጽ ፓርቲው ያቀረበውን ቅሬታ ተቀባይነት የሌለው ክስ ነው ብሏል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኔ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም 6ኛ ጠቅላላ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ጨምር የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ10 በላይ የክልል ምክርቤት ወንበሮች አግኝቷል፡፡ 3 የክልልና አንድ የፓርላማ ወንበር ያገኘው የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲም በተደጋጋሚ ጫናዎች እየደረሱበት እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ፀሀይ ጫኔ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW