1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ በትግራይ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2016

የሰላም ስምምነቱ በሙሉእነት እንዲተገበር ሀገራት ጫና እንዲፈጥሩ በትግራይ የሚገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጥሪ አቀረቡ። የአስር ሀገራት ዲፕሎማቶች በመቐለ ተገኝተው ከክልሉ ፖለቲከኞች ጋር ተወያይተዋል። በመቀለ ከተገኙት መካከል በኢንግሊዝ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከብሪታንያ የመጡ16 ስድስት ሃገራት ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

የትግራይ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዲፕሎማቶች በመቐለ
የትግራይ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዲፕሎማቶች በመቐለምስል Arena Tigray Party

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ በትግራይ

This browser does not support the audio element.

የሰላም ስምምነቱ በሙሉእነት እንዲተገበር ሀገራት ጫና እንዲፈጥሩ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጥሪ አቀረቡ። የአስር ሀገራት ዲፕሎማቶች በመቐለ ተገኝተው ከክልሉ ፖለቲከኞች ጋር ተወያይተዋል።

ሰሞኑን በመቐለ ግብኝት እያደረኩ ካሉ እና ከተለያዩ በትግራይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ከተወያዩት መካከል በኢንግሊዝ ኤምባሲ አስተባባሪነት ከብሪታንያ ሮያል ዲፌንስ ኮሌጅ የመጡ የአስር ሀገራት፥ አስራ ስድስት ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

ትላንት ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በትግራይ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ጋር የተወያዩት እነዚህ ዲፕሎማቶች በተለይም የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በሙሉእነት እንዲተገበርሁኔታዎች እንዲፈጥሩ ከፖለቲከኞቹ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ከዲፕሎማቶቹ ጋር ከተወያዩ መካከል የሆኑት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉ በትግራይ ያለው ሁኔታ ለማስረዳት፣ የሰላም ስምምነቱ በሙሉእነት እንዲፈፀም በፈራሚዎቹ ላይ ጫና እንዲፈጥሩ መጠየቃቸው ገልፀውልናል። 

ከዚህ ውጭ ላለፉት ሶስት ቀናት በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት ያደረገው በእስራኤል ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ የተመራ የእስራኤል ልኡክ በበኩሉ በትግራይ ያለው የከፋ ሰብአዊ ሁኔታ ለማቃለል በሚደረግ ጥረት መንግስታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

ምክትል አፈጉባኤ ሙሼ ሰለሙን በትግራይ ክልል ዓዲ ዳዕሮ የሚገኘው በጦርነቱ የወደመ ሆስፒታል ከጎበኙ በኃላ ለመገናኛ ብዙሐን በሰጡት አስተያየት እስራኤል በተለይም በሰብአዊ ጉዳዮች ዙርያ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። 

ምክትል አፈጉባኤው "እንዳየሁት በትግራይ ያለው ሁኔታ መጥፎ ነው። ዓለምም ሊያውቀው ይገባል። የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር አነጋግረን ድጋፍ ለማድረግ እንሞክራለን። አሁን ላይ እዚህ ሆኞ ይህ እናደርጋለን፣ ይህ እንፈፅማለን ማለት እንኳን ባልችልበሰብአዊ ጉዳዮች ዙርያ ለመስራት፣ በዛ ለመጀመር እንፈልጋለን" ብለዋል። ይህ

በእንዲህ እንዳለ አስተያየታቸው የሰጡን የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሀይሉ፥ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ልዩ ልኡካን እና ዲፕሎማቶች ከህወሓት ውጭ ሌሎች የትግራይ የፖለቲካ ሀይሎች ማነጋገር ሀሳባቸው መስማት መጀመራቸው በራሱ መልካም ውጤት ይዞ ሊመጣ የሚችል ብለውታል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

አዜብ ታደሰ

ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW