1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

የ 2024 ን የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ማን ያሸንፍ ይሆን?

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26 2017

ማን ያሸንፍ ይሆን? በዩናይትድ ስቴትስ አገር አቀፍ ምርጫ ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሐሪስ አንገት ለአንገት ተያይዘዋል ። ምርጫውን በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስዋሽንግተን ዲሲ እና ከአትላንታ የቀጥታ ሥርጭት ቃለ መጠይቆች አድርገናል ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች - 2024
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች - 2024ምስል David Swanson/Mike Blake/REUTERS

ቃለ-መጠይቅ፦ ስለ አሜሪካ ምርጫ ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ጋር

This browser does not support the audio element.

በዩናይትድ ስቴትስ አገር አቀፍ ምርጫ  ዛሬ ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሐሪስ አንገት ለአንገት ተያይዘዋል ። ምርጫውን በተመለከተ ከዩናይትድ ስቴትስዋሽንግተን ዲሲ እና ከአትላንታ የቀጥታ ሥርጭት ቃለ መጠይቆች አድርገናል ። በቀጥታ የምናመራው ወደ ዋንሽንግተን ዲሲ ነው ። የዋሽንግተን ወኪላችን አበበ ፈለቀ እንዳለው ከሆነ፦ ምርጫው ካማላ ሐሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ አንገት ለአንገት የተያያዙበት ነው ። የአትላንታ ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ በበኩሉ፦ ጆርጂያ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ነጩ ቤተመንግሥት ለማቅናት ዋነኛ የመፋለሚያ አውድማ ናት ብሏል ።  እንዴት? መልሶቹን ከቃለ መጠይቆቹ እናገኛለን ። 

ቅድሚያ ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ባለፈው ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ አውታር የወጣ ቪዲዮ ዶናልድ ትራምፕን ለመምረጥ የፈለገ መራጭ ማሽኑ እያዘለለ ካማላ ሐሪስን ሳይፈልግ ሲያስመርጠው ያሳይ ነበር ። እንዲህ አይነት እንከኖች ቢኖሩ ችግሩን ወዲያው ለመቅረፍ ዝግጅቱ ምን ይመስላል ለሚለው ጥያቄ፦ አበበ ፈለቀ ሲመልስ አንዳንድ ክስተቶች ችግር እንዳይፈጥሩ ወዲያውኑ መፍትኄእየተሰጣቸው መሆኑን ገልጧል ። የዴሞክራቶቹም ሆኑ የሪፐብሊካን ታዛቢዎች በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በበቂ ሁኔታ እንደሚታዩም አክሏል ። 

የአሜሪካ ምርጫ ውጤትን በዋናነት ከሚወስኑት ሰባት የአሜሪካ ግዛቶች መካከል አንዷ በሆነችው በጆርጂያ ግዛት የአታላንታ ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ በበኩሉ፦ ምርጫውን ዞር ዞር እንደተመለከተው ከሆነ ገና ከጠዋቱ አንድ ሰአት ነው ድምፅ አሰጣጡ የጀመረው ።  በዩናይትድ ስቴትስ የዴሞክራቶች እና የሪፐብሊካኖች የሚባሉ ግዛቶች እንዳሉ ይታወቃል ። ጆሮጂያ ከሰባቱ ስዊንግ ስቴት ወይንም ለሪፐብሊካንም ለዴሞክራትም ሊሆኑ ከሚችሉ ግዛቶች አንዷ ናት ። ታሪኩ ተዘዋውሮ በተመለከተው መሠረት የኢትዮጵያውን መራጮች ፍላጎት ምን እንደሆነም አብራርቷል

ሙሉ ቃለ መጠይቆቹን ከድምፅ ማእቀፎቹ ማድመጥ ይቻላል ። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አበበ ፈለቀ

ታሪኩ ኃይሉ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW