1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የ H1N1 ቫይረስ ስርጭት ና የዘንድሮው የሀጂና ዑምራ ጉዞ

ሰኞ፣ ሐምሌ 20 2001

በዓመት ከሁለት እስከ ሶሶት ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች ለሀጂና ዑምራ ጉዞ በሚጎርፉባት በሳውዲ አረቢያ H1N1 የተባለው ቫይረስ የሚያስከትለውን የአደገኛ ጉንፋን ስርጭት ለመቋቋም አስፈላጊውን ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን መንግስት አስታውቋል ።

የሜካ ተሳላሚዎች፣ምስል፦ AP

ከዚሁ ጋርም መንግስት ነፍሰ ጡሮች ህፃናት አዛውንትና አቅመ ደካሞች የዘንድሮውን የሀጂና ኡምራ ጉዞ ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉም አሳስቧል ። H1N1 የተባለው ቫይረስ በሚያስከትለው ከባድ ኢንፍሉዌንዛ የተያዘ አንድ ሰው ሳውዲ አረቢያ ውስጥ መሞቱ ዛሬ ይፋ ሆኗል ። በግል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ የቆየው ይኽው ሰው በካባዱ የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሞተ የመጀመሪያው ሰው መሆኑ ነው ። በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ በዚህ በሽታ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከ 300 በልጧል ። በሌላም በኩል በበሽታው ስርጭትና ቁጥጥር ላይ የተነጋገሩት የአረብ አገራት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮች በዘንድሮው የሀጂና ኡምራ ጉዞ የሚሳተፉ ሰዎችን ዕድሜ ገድበዋል ። ነብዩ ሲራክ ከጀዳ--

ነብዩ ሲራክ ፣ ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW