የ2013 ግንቦት ወር የምርጫ ዝግጅት
እሑድ፣ የካቲት 14 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ያደናቀፈውን ምርጫ ዘንድሮ ለማካሄድ ሦስት ወራት ገደማ ቀርተዋል። በምርጫው የሚሳተፉ ጥቂት የማይባሉ ፓርቲዎች የሚለዩበትን አርማ መርጠው፣ እጩዎችንም እያስመዝገቡ ለምርጫ ቅስቀሳዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በአንጻሩ እጩዎቻችን እና አባላቶቻችን ታስረዋል፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽሕፈት ቤቶችን ተዘግተዋል፤ በዚህ ሁኔታ በምርጫው እንዳንሳተፍ እየተገፋን ነው የሚሉም አሉ። ገዢው ፓርቲ በበኩሉ ከዚህ ቀደሙ የተሻለና የተለየ ምርጫ እንዲካሄድ የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ይናገራል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።
ሸዋዬ ለገሠ