በአዲሱ ዓመት የኢትዮጵያውያን ተስፋ
ዓርብ፣ ጳጉሜን 3 2015ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ ባልተረጋጋው የፖለቲካ ሁኔታ የሰላምመናጋት እና የኑሮ አለመረጋጋት ነዋሪዎችን ሲፈትን፤ በርካቶችንም ሲያስጨንቅ መስተዋሉ የተለመደ ጉዳይ እየሆነ የመጣ መስሏል። በ2010 ዓ.ም. በመሃል የታየው መረጋጋት እና የለውጥ ስሜት እምብዛም ሳይዘልቅ አንዴ በታዋቂ ግለሰቦች ግድያ በሌላ ጊዜ ደግሞ ንጹሐን ላይ በሚፈጸሙ የጅምላ ግድያ እና ግጭቶች የተነሳ ተስፋዎች እየደበዘዙ ውጥረት ስፍራውን ሲይዝ ተስተዋለ። በተለይም ደግሞ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ ክልል የፈነዳው የከፋው የእርስበርስ ጦርነት ለድፍን ሁለት ዓመታት ዘልቆ በ2015 ዓ.ም. መጀመሪያ መቋጫ ቢያገኝም ትላልቆቹ የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች፤ ብሎም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የግጭትና ግድያ ዜናዎችን መስማት እንደቀጠለ ነው። ኢትዮጵያ አሮጌውን 2015 ዓ.ም. ሸኝታ አዲሱን 2016 ዓ.ም. ለመቀበል ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋታል። ኢትዮጵያውያንም ስለአዲሱ ዓመት መልካሙን ማለም ጀምረዋል፡፡ ለመሆኑ በአዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ ምን ይከሰት ይሆን? አዲሱ የኢትዮጵያውያን ዓመት አገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በከፋ መልኩ እየተፈተነችበት የመጣችውን የግጭት ሰቆቃዎችን የምትገላገልበት ይሆን? የተወሰኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ጠይቀናል።
ሥዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ