1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

ሰኞ፣ ጥቅምት 17 2018

የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ጌትነት ወርቁ፤ ነገር ግን መንግሥት በሐገሪቱ ሰላም ካስከበረ፤ ጦርነቶች ቆመው፣ የታሰሩት ተፈትተው፣ ያኮረፉት ኃይሎች ጋር የውይይትና የድርድር ሁኔታዎች ከተካሄዱ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ተስፋቸውን ይገልጻሉ።

መራጭ ድምጽ ሲሰጡ (ከፎቶ ማሕደራችን የተወሰደ)
መራጭ ድምጽ ሲሰጡ (ከፎቶ ማሕደራችን የተወሰደ)ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

የታገደ ፓርቲ አድራጊ ፈጣሪ በሆነበት ሁኔታ አስቻይ ሁኔታ እንዴት ይኖራል?

This browser does not support the audio element.

 የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ዓምን ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። ዶቸቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰጡት አስተያየት በበኩላቸው በሀገሪቱ በአሁን ሰዓት ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ይናገራሉ። ለማሳያነትም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ፣ የተመጣጣኝ ድምፅ የምርጫ ሥርአት በምክርቤት አለመጽደቅ፤ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞች እስርና ወከባን ጠቅሰዋል። 

የ2018 ምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስጋት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ዓ.ም የምርጫ የጊዜ ሰሌዳን በተመለከተ ጥቅምት 10 ቀን 2018  ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በዝግ መክሯል። ቦርዱ በቴሌግራም ገጹ ባሰራጨው መግለጫ መጪውን ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ በተያዘው ዓመት ለማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አመልክቷል። ረቂቅ የጊዜ ሰለዳው የምርጫ ጽሕፈት ቤቶችን ከማደራጀት እስከ ይፋዊ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ድረስ መሆኑን ያሳያል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ግን በሐገሪቱ አለ ያሉትን የጸጥታ ችግርና ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ያስረዳሉ። 

« ከምርጫው እራሳችንን እናገላለን» (የገዳ ቢሊሱማ ኦሮሞ ፓርቲ)

የገዳ ቢሉስማ ኦሮሞ ፓርቲ ባሰራጨው መግለጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የተስማሙበትን ባገኙት ድምፅ የሚወከሉበት የተመጣጣኝ ድምፅ የምርጫ ሕግ በምክርቤት ጸድቆ ሥራ ላይ ካልዋለና በፓርቲው ላይ የሚደርሰው ተፅዕኖ ካልቆመ ከምርጫው እራሱን ለማግለል እንደሚገደድ አስታውቋል። የድርጅቱ የበላይ ሀላፊ አቶ ሮበሌ ታደሰ ለዶቸቨቬ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የታገደ ፓርቲ አድራጊ ፈጣሪ በሆነበት ሁኔታ አስቻይ ሁኔታ እንዴት ይኖራል?

 አቶ ከበደ አሰፋ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሰብዓ እንደርታ ፖርቲ ሊቀመንበር ናቸው። በትግራይ ያለው ውስብስብ የፖለቲካ ችግር ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ አደለም ባይ ናቸው። በተለይም በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የታገደውህወሐት የጸጥታና የመንግሥት መዋቅሩን ተቆጣጥሮ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ፓርቲዎችና ግለሰቦች በሚያሳድድበት ክልል ውጤታማ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት እንደሌላቸው ያስረዳሉ።

መራጮች የምርጫ ውጤት ሲከታተሉ (ከማሕደራችን የተወሰደ ፎቶ)ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

«ቀጣዩ ምርጫ የመሠራት ወይም የመሰበር አድርገን ነው የምንወስደው»

 «አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ለማካሄድ አይደለም ስለምርጫ ለመወያየትም ቅንጦት ነው» በማለት ሐሳባቸውን የጀመሩት የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ጌትነት ወርቁ፤ ነገር ግን መንግሥት በሐገሪቱ ሰላም ካስከበረ፤ ጦርነቶች ቆመው፣ የታሰሩት ተፈትተው፣ ያኮረፉት ኃይሎች ጋር የውይይትና የድርድር ሁኔታዎች ከተካሄዱ ምርጫው ሊካሄድ እንደሚችል ተስፋቸውን ይገልጻሉ። ለዚህም ፓርቲያቸው በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን በማከል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢህአፓ/ ዋና ጸሐፊና አሁን የፓርቲው አባል የሆኑት ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ወይዘሮ ደስታ ጥላሁን ፓርቲያቸው በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ይገልጻሉ። ይሁንና ስጋት አለን ይላሉ ወይዘሮ ደስታ።
ድምጽ 4 

ፓርቲዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ተአማኒ፣ ፍትሀዊና ቅቡልነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ ከተፈለገ በቅድሚያ በመላ ሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግና «ያኮረፉ» ያሏቸውን ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል። 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW