1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የ2023 የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ፈተና በአፍሪቃ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 18 2016

ባለሰማያዊ ኮፍያወቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በጎርጎሪያኑ 2023 ዓ/ም በአፍሪቃ ያስመዘገቡት ስኬት አነስተኛ ነው።በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጠረው ግጭት ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። እንደ አለመታደል ሆኖ፣የሰላም አስከባሪ ሀይሉ በማሊም ስኬታማ አልነበረም። የተልዕኮው ውድቀት ዋና መንስኤ ምን ይሆን?

የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በማሊ
የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በማሊምስል፦ SIA KAMBOU/AFP

የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ የ2023 ተግዳሪቶች በአፍሪቃ

This browser does not support the audio element.

 

ባለሰማያዊ ኮፍያወቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች  በዚህ ወር አጋማሽ በባማኮ በሚገኘው MINUSMA የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዋና መሥሪያ ቤት መደበኛ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።ይህም ከ53 ሀገራት የተውጣጡ ወታደሮችን ያሳተፈው ተልዕኮ ፍጻሜ ሆኗል።

እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ደቡብ ሱዳን እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባሉ ሀገራትም የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች እየተገባደደ ባለው የጎርጎሪያኑ 2023 ዓ/ም ብዙም ስኬት አላስመዘገቡም። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት በእነዚህ ሀገራት ውስጥ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥብቅ  መመሪያዎችን በመከተሉ ተልዕኮዎቹ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። የጃቲካይ ሴንተር ዳይሬክተር የሆኑት አዲብ ሳኒ በቅርብ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች በአፍሪካ አንዳንድ ክፍሎች እያሳየ ያለው ደካማ አፈፃፀም ቅር መሰኘታቸውን ይገልፃሉ።

«በከፍተኛ ደረጃ፣ ወደዚያ ቦታ ለመምጣት ምክንያት የሆናቸውን እና በእነዚያ ሀገሮች ውስጥ ያለውን የዓመፅ አዙሪት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መከላከል አልቻሉም። ለዚህ ግልጽ ማሳያ የሚሆነው መፍትሄ ያላገኘችው ማሊ ነች። ምክንያቱም ከቀን ወደ ቀን ብጥብጡ እየተባባሰ የመጣ ይመስላል፣ እናም ተልዕኮው ምንም ፋይዳ የሌለው ይመስላል።»

የመንግስታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ከሰፈረባቸው ሀገሮች አንዷ በሆነችው ማሊ፤ባለፈው ሰኔ ወር አጋማሽ የሀገሪቱ  ወታደራዊ መንግስት ከሩሲያ ጦር ጋር ያለውን ትብብር ከጨመረ ወዲህ፤12,000 የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ለቀው እንዲወጡ ጠይቋል።ከዚህ በተጨማሪ የማሊ ባለስልጣናት የመንግስታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሀገሪቱ ያለውን አደገኛ የጸጥታ ሁኔታ በበቂ ሁኔታ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ "የችግሩ አካል" ሆነዋል ሲሉም  ከሰዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በማሊምስል፦ Nicolas Remene / Le Pictorium/IMAGO

 አዲብ ሳኒ ግን፤ እንደ ማሊ ያሉ መንግስታትም የተልዕኮዎችን እንቅስቃሴ አደጋ ላይ በመጣል ሃላፊነት አለባቸው ይላሉ። «ታውቃላችሁ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ የሚሳካው እነሱ በሚንቀሳቀሱበት ምህዳር ውስጥ ጠንካራ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ሲኖር ብቻ ነው። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት ከሌለ ለእነሱ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል።ለምሳሌ እንደ ማሊ በወታደሩ በነበረት ወቅት በጣም ያልተረጋጋ ሀገር ነበረች። ስለዚህ የተባበሩት መንግስታት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ መንቀሳቀስ መቻል በጣም ፈታኝ ይሆናል። በሁለተኛ ደረጃ  በሂደቱ ላይ ብዙዎች እምነት እንዲኖራቸው መሰራት አለበት።» 

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች እንቅስቃሴያቸውን በሚገድቡ ግልጽ የስራ ማስፈፀሚያ  ትዕዛዞች የሚሰሩ በመሆናቸው ተልዕኮው አስገዳጅ  ማስፈጸሚያ የለውም። ከዚህ አንፃር እራስን እና የተሰጣቸውን ስልጣን ለመከላከል ካልሆነ በቀር  ሃይል መጠቀም አይፈቀድላቸውም። እንደ ፊዴል አማኪ ኦውሱ ያሉ አንዳንድ ተንታኞች ይህንን መሰሉን   “ደካማ” የሰላም ማስከበር ኃላፊነት ለተልዕኮው አለመሳካት ተጠያቂ ያደርጋሉ።

የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በማሊ በጎርጎሪያኑ 2021 ምስል፦ Nicolas Remene / Le Pictorium/IMAGO/MAXPPP/dpa/picture alliance

«በአፍሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች በሙሉ እየከሸፉ ነው አልልም። ይልቁንስ እንዲሰሩ በተፈለገባቸው አካባቢዎች ውጤታማነታቸውን የሚገድበው የተሰጣቸው ተልዕኮ ባህሪ ነው። በእርግጥ፣ የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮዎች የተወሰኑ መመሪያዎች፣ የተወሰኑ ግዳጆች ስላሏቸው ፤ ከዚህ ውጭ መሄድ አይችሉም። በአፍሪካ ውስጥ ያሉ የግጭት ሁኔታዎች ደግሞ በጣም ተለዋዋጭ እና  ያማይገመቱ በመሆናቸው፤ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪቃን ግጭት በአንድ ላይ ለማስተናገድ አስቸጋሪ ያደርገዋል። ስለዚህ በአብዛኛው የቻሉትን ሁሉ ያላደረጉ ያስመስላቸዋል።»

ይሁን እንጂ ሰላም አስከባሪ ሃይሎች በተቀባይነታቸው የአገራቸውን አመኔታ ለማግኘት ብዙ ጥረት አላደረጉም።አንዳንዶቹ በፆታዊ ጥቃት እና በደል ተከሰዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 60 የታንዛኒያ ሰላም አስከባሪዎችን የያዘው ክፍል በዚህ አመት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በፆታዊ ጥቃት እና በደል ክስ ወደ ሀገር ቤት ተልኳል።
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ የተልዕኮው ወታደሮች በሚንቀሳቀሱባቸው አንዳንድ ሀገሮች ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ነው። 
ስለሆነም በአፍሪካ በሚቀጥሉት አመታት ስኬታማ ለመሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮዎች ላይ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይከራከራሉ።

 

ፀሀይ ጫኔ
ሂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW