የ2023 የጅቡቲ የእንደራሴዎች ምክርቤት ምርጫ
ሰኞ፣ የካቲት 20 2015
ጅቡቲ በአለፈው ዓርብ የምክር ቤት አባላት ምርጫ አካሂዳለች። በምርጫው ከአንድ በስተቀር የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዳልተሳተፉ ሪፖርቶች ያመላክታሉ። 65 መቀመጫ ላለው ወንበር በተካሄደ ምርጫ ከሰባቱ በስተቀር ገዚው ፓርቲ እንዳሸነፈ እየተነገረ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ሂደቱን በቅርበት የሚከታተሉት የዓፋር ሰብአዊ መብት ድርጅት የበላይ ሐላፊ ከሆኑት አቶ ጋዓስ አሕመድን አነጋግረናቸዋል። እንደ አቶ ጋዓስ ገለጻ ጎረቤት ሃገር ጅቡቲ ከዓመት በፊት ፕረዚደንታዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን አሁን ዓርብለት የተካሄደው ምርጫ ደግሞ የእንደራሴዎች ምክርቤት ምርጫ ነው።
በዚህ ምርጫ እንደሳቸው አገላለጽ የመንግስት ተለጣፊ ከሆነ አንድ ፓርቲ በስተቀር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው እራሳቸውን አግልለዋል።
እስከ አሁን ይፋዊ ያልሆኑ የምርጫ ውጤቶች እንዳመላከቱት ከ65 መቀመጫዎች ከሰባቱ በስተቀር ሁሉንም ወንበሮች ገዢው ፓርቲ ጥርግርግ አድርጎ ``እንዳሸነፈ`` ይገልጻሉ አቶ ገዓስ።
ጅቡቲ በተለይ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ እንደምትገባ በማስረጃ የተደገፉ ሪፖርቶች ለፌደራልና ለዓፋር ክልል መንግስት ማቅረባቸውን የገለጹት አቶ ጋዓስ ይሁንና ተድበስብሶ እንዳለፈ ለDW ተናግሯል።
የአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚዎችና አማራጭ ሐሳብ ያልቀረበበት ነው ያሉት አቶ ጋዓስ የነበረው አገዛዝ ስለሚቀጥል በውጭ ግኑኝነት በኩል የሚሻሻል ነገር እንደማይኖር ተናግረዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ