1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ51 ተከሳሾች የክስ ጭብጥ በዐቃቤ ሕግ ተሻሽሎ ቀረበ

ሰለሞን ሙጬ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 3 2017

ዛሬ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የተሰየመው ችሎት ከተከሳሾች መካከል አራቱ በሕመም ምክንያት ባለመቅረባቸው ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ ሁሉም ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ለሕዳር 5 እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል። የተከሳሽ ጠበቆች ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ መቃወሚያ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

Äthiopien | Justiz
ምስል Solomon Muchie/DW

በሃምሳ አንዱ ተከሳሾች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው ክስ

This browser does not support the audio element.

51 ተከሳሾች የክስ ጭብጥ በዐቃቤ ሕግ ተሻሽሎ ቀረበ

 

አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች የክስ ጭብጥ ተሻሽሎ ቀረበ።

ዛሬ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የተሰየመው ችሎት ከተከሳሾች መካከል አራቱ በሕመም ምክንያት ባለመቅረባቸው ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ ሁሉም ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ለሕዳር 5 እንዲቀርቡ ቀጠሮ ሰጥቷል። የተከሳሽ ጠበቆች ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ መቃወሚያ እንደሌላቸው ገልፀዋል። 

በዛሬው ችሎት በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ተከሳሾች መካከል መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ አራት ተከሳሾች አልቀረቡም።

በፖሊስ ተይዘው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው ጥቂት ወራት የቀራቸው በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ሥር በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ሰዎች፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ክስ ማሻሻያ እንዲያደረግበት ያቀርቡት የነበረው ጥያቄ አንዱ የችሎቱ መከራከሪያ ጉዳይ ነበር።

የፖለቲከኞች ከእስር መለቀቅና የእነዶ/ር ወንድወሰን የፍርድ ቤት ውሎ

ዛሬ በዋለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ዐቃቤ ሕግ ይህንን የተከሳሾችን የክስ ይሻሻል ጥያቄ ተቀብሎ ክሱን አሻሽሎ መቅረቡን ከተከሳሽ ጠበቆች አንደኛው ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

ዛሬው ችሎት በማረሚያ ቤት ከሚገኙት ተከሳሾች መካከል መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ አራት ተከሳሾች አልቀረቡም።ምስል Solomon Muchie/DW

"ዐቃቤ ሕግ የተሻሻለ ክሱን ወደ 68 ገጽ የሚጠጋ አሸሽሎ አቅርቧል።" ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ይህንን ክስ ይሻሻል የሚል አቤቱታ በተመለከተ ጉዳዩን ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ይዞት ሄዶ የነበረ ሲሆን ምክንያት በሚል ያቀረበው "የሟቾች ስም እና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቢዘረዘር በተለይም ምስክር ከሆኑት ላይ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል"፣ ስለሆነም ክሱን ላሻሽል አይገባም የሚል ነበር። ሆኖም በዛሬው ችሎት ሰበሩ ሰሚ ላይ የቀረበው ጉዳይ ውሳኔ ወይም መቋጫ ሳያገኝ ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ጠበቃ ሔኖክ ተናግረዋል።

የእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፣ የእነ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ የተፈቀደ ዋስትና ዛሬም አልተከበረም

"ፍርድ ቤቱ ያልተማሉ ተከሳሾች ስላሉ እነሱ ይሟሉ እና ቃላችሁን ትሰጣላችሁ በሚል ለሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶበታል።" በሌላ በኩል በዚሁ መዝገብ ያልቀረቡ ተከሳሾች ላይ በጋዜጣ የተደረገውን ጥሪ ውጤት ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቶት የነበረው ዐቃቤ ሕግ ፖሊስ ጥሪ የደተደረገላቸውን ሰዎች ማቅረብ እንዳልቻለ በመግለጽ ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ይህንን በተመለከተ በቀጣይ ሊሆን የሚችለው ሂደት ምን እንደሆነ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉን ጠይቀናል።

"በከሱ ላይ በርካታ ተከሳሾች ነው ያሉት። ያልመጡ አሉ፣ ያልተያዙ አሉ፣ ውጭ አገር የሚገኙ አሉ፣ በረሃ ላይ ደግሞ ያሉ አሉ።" በማለት ጉዳዩ በችሎቱ ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በፌደራል ዐቃቤ ሕግ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች "የፖለቲካ እና የርዕዮት አላማን ለማራማድ በማሰብ የሽብር ድርጊት ፈጽመዋል" በሚል ነው ክስ የቀረበባቸው።51 ዱ ሰዎች በአማራ ክልል በመንቀሳቀስ መንግሥትን ለመጣል የፖለቲካ ዓላማ ይዘው እንቅስቃሴ አድርገዋል፣ በዚህ ሂደት በንፁሃን ሰዎች ላይ፣ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል የሚል ሰፊ የክስ ጭብጥ ቀርቦባቸዋል። 

በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች ችሎት

በቃሊቲ እና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች በእሥር ላይ ከሚገኙት ተከሳሾች መካከል በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ይሠሩ የነበሩት መስከረም አበራ፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ዳዊት በጋሻው እና ገነት አስማማው በዚህ የክስ መዝገብ ውስጥ ይገኙበታል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW